ዋሺንግተን ዲሲ —
የማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ለመንገደኞች ሰለቫይረሱና ስለሚተላለፍባቸው መንገዶች መረጃ እንደሚሰጥና በዓለም የጤና ድርጅት ምክር መሰረትም ቦሌ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ የሰውነት የሙቀት መጠን ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።
ቫይረሱና የሚያስከትለውም ህመም ወደታየባቸው አካባቢዎች የሚጓዙ መንገደኞች፣ የሳልና የትኩሳት ምልክት ከሚታይባቸው ሰዎች እንዲርቁ፣ በአመጋገብና በግል ንፅህና አጠባበቅ ላይም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ የኢትዮውያን የመከላከልና የዝግጅነት ሥራ የሚያስተባብረው የማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መክሯል።
የዓለም የጤና ድርጅትም ትናንት በሰጠው መግለጫ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምቀፍ ሥጋት መደቀኑን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ከቻይና ውጭ የጤና አደጋ ነው ብሎግን አላወጀም።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ