ዋሺንግተን፤ ዲሲ —
አቶ ዳውድ ኢብሳ
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ “ከመቼውም ጊዜ በላይ የተወሳሰበ ነው” ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አጠቃላይ የሃገራዊ ንግግር መድረክ እንዲጠራ ጠይቋል።
ግንባሩ ህዳር 16/2012 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ “ችግሩን ይበልጥ በማስፋፋት ወደ ህዝቦች ግጭት ለመቀየር ሲሞክር እየታየ ነው” ብሏል።
የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።