ዋሺንግተን ዲሲ —
ፕሬዚዳንቱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጡት ትዊታቸው
“አሁን እየተገነባ ባለው ከዓለም እጅግ ግዙፍ ከሆኑት አንዱ በሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ለረዥም ጊዜ ለቆየ ውዝግባቸው መፍትኄ እንዲገኝ ለማገዝ ከግብፅ፣ ከኢትዮጵያና ከሱዳን ከፍተኛ ተጠሪዎች ጋር ያደረግነውን ስብሰባ አሁን ጨረስን፡፡ ስብሰባው የተካሄደው በመልካም ሁኔታ ነበር። ውይይቱ ቀኑንም ቀጥሎ ይውላል።” ብለዋል፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከግብፅና ከሱዳን አቻዎቹ ጋር የሚያደርገው ውይይት በፕሬዚዳንት ትረምፕ ግብዣ በገንዘብ ሚኒስትሩ ስቲቭን ምኑቺን አስተባባሪነት የሚካሄድ ሲሆን የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስም እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
የሦስቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የዋሽንግተን ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ የምትገኘው “ለምክክር እንጂ ለድርድር አይደለም” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ ቀደም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የስብሰባውን ሂደት በቅርብ እየተከታተልን መዘገባችንን እንቀጥላለን፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ