በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የታገቱ ተማሪዎችን አስመልክቶ የተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገDessie against the abduction of students from Dembi Dolo University
የኢትዮጵያ መንግሥት የታገቱ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በተመለከተ በቂ ትኩረት አልሠጠም ያሉ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተማዎች ዛሬ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል።
1494ኛው የነብዩ መሐመድ ልደት መውሊድ ሰሞኑን በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል።
“ይህን የፈጸሙ አካላት ለፍርድ ይቀርባሉ። የምንደራደረው ጉዳይ አይደለም። ዩኒቨርሲቲዎቻችን የምርምር ተቋማት እና የኢትዮጵያዊነት መለጫ ሞዴሎች ናቸው። ሰላም እንዲሆን እንፈልጋለን።የድንጋይ መወራወሪያ የጸብ ማጫሪያ የሴራ ማሰሪያ እንዲሆኑ አንፈልግም። የምርምር ተቋም ብቻ እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው።” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮምሽነር አበረ አዳሙ።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳይታ ዱብቲ አካባቢ የውጭ አገር መታወቂያና ተሽከርካሪ ይዘዋል የተባሉ ታጣቂዎች ከትላንት በስቲያ ሰነዘሩት በተባለው ጥቃት በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ትናንትና ከትናንት በስቲያ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ አካባቢና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች ተፈጥሮ የነበረው ውጥረት እየተረጋጋ መምጣቱን የፀጥታ ኃይሎችና ኅብረተሰቡ ገልፀዋል፡፡
ላለፍት 7 ቀናት ሲያካሂዱት የነበረውን ፀሎተ ምህላ ያጠናቀቁት በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ምዕመናን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ይፈፀማሉ ያሏቸው ጥቃቶች እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ላይ የመማር አቅም አጥተው የነበሩና በሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችን ለመርዳት በተቋቋመ “የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት” ድርጅት ታግዛ የፍተኛ ትምሕርቷን ያጠናቀቀችው መሰረት መራዊ “ስለ ትምሕርቴ ብቻ በማሰብ ለዚህ በቅቻለሁ” ትላለች።
ከ1ሰላሣ ሚሊዮን ብር በላይ ለግንባታ፣ ለመሣሪያዎችና ለግብአቶች ወጭ አድርገው በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጥረት ምክንያት ወደ ሥራ መግባት አለመቻላቸውን በደሴ ከተማ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሠማራት እንቅስቃሴ የጀመሩ ግለሰቦች ገልፀዋል።
በአማራ ክልል ያለፈው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ ወቅት “የቁጥጥር መላላት ነበር” የሚል ለክልሉ የትምህርት ቢሮም ለሃገር አቀፉ የፈተናዎችና ምዘና ኤጀንሲም የቀረበ ቅሬታ እንደሌለ የክልሉ የትምህር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ ገልፀዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ስር ያሉት የካቤና አካባቢው ቀበሌዎች ነዋሪዎች በቅርቡ ወደ አካባቢው ልዩ ኃይል በመስፈሩ ቅሬታ እንዳላቸው የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ከስድሣ ሚሊየን ብር በላይ የፈሰሰበት የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ፋብሪካ ሰሞኑን አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች በራሳቸው ተነሳሽነት የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳት ላይ ይገኛሉ።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በደሴና አካባቢዋ የህፃናት ሥርቆት እየተባባሰ መምጣቱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተከስቶ የነበረው መረጋጋት ቢስተዋልበትም ተመልሶ ላለማገርሸቱ ምንም ዓይነት ማስተማመኛ የለንም ሲሉ ተማሪዎቹ ሥጋታቸውን ገልፀዋል።
ዛሬ በደሴ ከተማ መምህራን ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተቀሰቀሱ ግጭቶችና አለመረጋጋት ወደ ዋግ ኽምራ አስተዳደር ዞን ጋዝ ጊብላ ወረዳ የመጡ ተፈናቃዮች ያለምንም ዕርዳት መቆየታቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
በወሎ አካባቢ የሚኖሩና የእስልምና ዕምነት ተከታይ ያልሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ባለፈው አርብ ሙስሊም ወንድሞቻቸውን ራማዳንን ፆም አስፈትተዋል ወይም አስፈጥረዋል።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲተዳደሩ የቆዩ ሦስት ወረዳዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ የክልሉ ገዥ ፓርቲ በቅርቡ ያሳለፈውን ውሳኔ የሚጋሩ ድጋፋቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ