ደሴ —
በ1771 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ የዘለቀው ስኮትላንዳዊው አገር አሳሽ ጀምስ ብሩስ በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ጎንደር አካባቢ ከፍተኛ ወረርሽኝ ተከስቶ ለበርካቶች ሞት ምክንያት መሆኑን ዘግቧል፡፡
በ1860ዎቹም ፈንጣጣ ብዙዎችን ገድሎ የብዙዎቹን አካል አጉድሎ ጠባሳውን ጥሎ እንዳለፈ ፈረንሳዊው አርኖልድ ዲ አባዲ ዘክሮታል፡፡
በአገረኛው አጠራር የህዳር በሽታ የሚባለውና ከአዲሱ ኮሮናቫይረስ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ስፓኒሽ ፍሉ የሚባል በሽታ የዛሬ መቶ ዓመት ገደማ ተከስቶ ያደረሰውን መጠነሰፊ ጉዳት አገራዊ ሰነዶች ሰንደው ይዘውታል፡፡
ወረርሽኞቹ የከፋ የህይወት መስዋእትነት እንዳያስከፍሉ ቤተ እምነቶችና የኃይማኖት አባቶች የራሳቸውን ኃላፊነት ተወጥተዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ