በወሎ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም ቀጥሏል። በግጭቱ ጉዳት ደርሷል። በአማራና በኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጆች መካከል መካረር ተፈጥሮ ግጭት እንዳይከሰት የኃይማኖት አባቶች በተማሪዎች መካከል ተገኝተው ምክር ሰጥተዋል።
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች የተለያዩ ከተሞች ሰሞኑን ለተመፀመው ጥቃት ግጭቱን የቀሰቀሰው ማነው? ነዋሪዎች፣የዞኑ አስተዳዳሪዎች፣ የአብን እና የግንቦት ሰባት አመራሮች አስተያየት ተጠይቀዋል።
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተከሰተው ጦርነት ፖለቲካዊ ቀውስን ያስከተለ ማኅበራዊ ጠባሳ የፈጠረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ በዘር በኃይማኖት አንድ የነበረ ህዝብ በማይታይ አጥር ተከልሎ በናፍቆት ሰቀቀን ሁለት አሥርት ዓመታትን ተሸግሯል፡፡
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል አጎራባች ወረዳዎች ግጭት መከሰቱን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ላለፉት አራት ዓመታት በደሴ ከተማ አስተዳደርና በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ፈቃደኛ የትምህርት ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ምዘና ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡
በአማራ ክልል የመጀመሪያው የሆነውና በደሴ ከተማ የተገነባው ይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ አዳሪ ት/ቤት ትናንት ተመርቋል፡፡
"ሁሉ ነገር ድሮ ቀረ" የሚሉ ወገኖች አጥብቀው ከሚሟገቱባቸው አጀንዳ ውስጥ ቀዳሚው የግብረገብነት ጉዳይ ነው፡፡
በመሰረቱ እጥረት ሳይኖር አንዳንድ ግለሰቦች ሆን ብለው በማገት የሚፈጥሩት የነዳጅ እጥረት በደሴ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው፡፡