በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮቪድ-19 ህይወቱ ያለፈን ግለሰብ የቀብር ሥነ ስርዓት የታደሙ ወደ ለይቶ ማቆያ ገቡ


ከደሴ መንገድ አዲስ አበባ መንገድ
ከደሴ መንገድ አዲስ አበባ መንገድ

በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ በኮቪድ-19 ህይወቱ ያለፈን ግለሰብ ተሰባስበው የቀበሩ 57 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደረገ፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እንዳስታወቀው ግለሰቡ አደጋ ደርሰበት ህይወቱ ቢያልፍም በተደረገለት የናሙና ምርመራ ቫይረሱ እንዳለበት ተረጋግጧል፡፡

የናሙና ውጤት የወሰዱ የጤና ተቋማት ውጤቱ ሳይታወቅ አስከሬን ለቤተሰብ የሚያስረክቡ ከሆነ ለቫይረሱ ስርጭት መባባስ ምክንያት ይሆናሉ ሲሉ የጤና ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኮቪድ-19 ህይወቱ ያለፈን ግለሰብ የቀብር ሥነ ስርዓት የታደሙ ወደ ለይቶ ማቆያ ገቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:37 0:00


XS
SM
MD
LG