ኢህአዴግ ከሌሎች ሃያ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ለማካሄድ በሚረዱ አሰራሮች ላይ ለመወሰን የሚያስችል ስምምነት ደረሰ።
ኢትዮጵያ ውስጥ በሦስት መቶ ወረዳዎች በሕፃናት፣ በእናቶችና በቤተሠብ ጤና ዙሪያ ሲከናወን የቆየ መረኃ ግብር ሰላሣ ሰባት ሚሊዮን ለሚሆን ሰው አገልግሎት መስጠቱ ተገልጿል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩ አባላቱና ደጋፊዎቹ መካከል ዛሬም ምንም ዓይነት ውሣኔ ያልተሰጣቸው እንዳሉ አስታወቀ፡፡ ከዘመዶቻቸውም ሆነ ከሕግ ጠበቃዎቻቸው ጋር ስለማይገናኙ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ መቸገሩንም ፓርቲው ገልጿል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እነ ማስረሻ ሰጤ ብሬ በሚል መዝገብ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ በ23 ታራሚዎች ግድያና በሽብር ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በዝግ ችሎት እንዲታይ ጠየቀ፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ መሪ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጋዜጣዊ መግለጭ ላይ ያስተላለፍዋቸው መልእክቶች የሀገሪቱን ወቅታዊ አጣዳፊ ሁኔታ ያገናዘቡ አይደሉም ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቀስቅሰው ከቆዩ ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ በአሥር ሺኾች የሚቆጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መቆየታቸውን፣ መንግሥቱ የአስተዳደር ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን፣ እንደ ግብፅ ካሉ መንግሥታት ጋር ውይይት መጀመሩን አስታውቋል።
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬ በፌስ ቡክ አድራሻው ያወጣቸው ፁሁፎች በሽብር ወንጀል የሚያስጠይቁኝ አይደሉም ሲል ቃሉን ለፍርድ ቤት ሰጠ።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የፌዴራሉ አቃቤ ሕግ በአሸባሪነት ክስ በመሰረተባቸው በነከድር መሐመድ ላይ እስከ አምስት አመት ተኩል የሚደርስ የእስር ቅጣት ጣለባቸው።
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በኢንተርኔት አምደኞቹ በነሶልያና ሽመልስና በአቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬም ብይን ለመስጠት እንዳልቻለ አስታወቀ።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ለሁለተኛ ጊዜ ተጨማሪ የ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰጦታል።
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ፣ በሃያ ሦስት ታራሚዎች ግድያና በሽብር ወንጀል አቃቤ ሕግ ክሥ የመሠረተባቸው ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ “ግፍ ፈፅሞብናል” ሲሉ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤት አሰምተዋል፡፡
ዶክተር መረራ ጉዲና ሰሞኑን ሲወራ እንደሰነበተው ሳይሆን ምንም ዓይነት የማሰቃየት ድርጊት አልትፈፀመባቸውም ሲሉ ጠበቃቸው አስተባበሉ።
ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ሃላፊነት እንደሆነ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ አሳሰቡ፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ ወቅቱ የኢትዮጵያ ችግር አጣዳፊ መፍትሔ የሚሻው ነው አሉ፡፡ እንደ መፍትሔ ካሉዋቸው መካከል አንዱና ዋነኝ ቁልፍ የሆኑ እስረኞች መፍታት ነው ብለዋል፡፡
የሃገር ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ የመላ ኅብረተሠቡ ኃላፊነት መሆን እንዳለበት አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን አስገነዘቡ፡፡
ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር በታሰሩ በአሥራ አምስተኛ ቀናቸው ዛሬ ከሕግ ጠበቆቻቸው ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ።
በደቡብ ወሎ አያሌ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች መታሠራቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር አስታወቁ።
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬም ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ ተገልጿል።
መሪው ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና መንግሥት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይትና ድርድር እንዲጀምር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ጥሪ አሰምቷል፡፡
ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ከዶ/ር መረራ ጉዲና ጋር ባለፈው ሳምንት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ወጣቶች ትላንት ማምሻውን መለቀቃቸው ተነገረ።
ተጨማሪ ይጫኑ