በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከተቃዋሚዎች ጋር እንደሚነጋገሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ


ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ

የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቀስቅሰው ከቆዩ ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ በአሥር ሺኾች የሚቆጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መቆየታቸውን፣ መንግሥቱ የአስተዳደር ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን፣ እንደ ግብፅ ካሉ መንግሥታት ጋር ውይይት መጀመሩን አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲካሄዱ ከነበሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችና አመፆች ጋር በተያያዘ ወደ ሃያ ሁለት ሺኽ የሚጠጉ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ውለው መቆየታቸውንና መንግሥትም የአስተዳደር ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል።

“የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል” በሚል የኢትዮጵያ መንግሥትና ተቋማት በተደጋጋሚ ክስ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የግብፅን አምባሳደር ጠርተው ማነጋገራቸውንና ከፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ኤል-ሲሲ ጋርም በከፍተኛ ደረጃ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

በሌላም በኩል ገዢው ፓርቲ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡ የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙርያ ለመከራከር እቅድ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ገልፀዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከተቃዋሚዎች ጋር እንደሚነጋገሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:50 0:00

XS
SM
MD
LG