በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ከሕግ ጠበቆቻቸው ጋር ተገናኙ


ዶ/ መረራ ጉዲና
ዶ/ መረራ ጉዲና

ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር በታሰሩ በአሥራ አምስተኛ ቀናቸው ዛሬ ከሕግ ጠበቆቻቸው ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ።

ዶ/ር መረራ ጉዲና ለብቻቸው በአንድ ክፍል የታሠሩ ቢሆንም በጤንነታቸው በኩል ደህና መሆናቸውን ጠበቃቸው ገልፀዋል።

ዶ/ር መረራ በሚቀጥሉት አሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ከሕግ ጠበቆቻቸው ጋር ተገናኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00

XS
SM
MD
LG