በኢንተርኔት አምደኞቹ በሶልያና ሽመልስና በአቃቤ ህግ መካከል ባለው ክርክር ውሣኔ ለማሰማት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዛሬም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና የትኛውንም የኢትዮጵያን ሕግ አልጣሱም ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ - ኦፌኮ መግለጫ አውጥቷል፡፡
“በአህጉራችን ስለፊደል ካስትሮ ያለው ስሜት ተመሣሣይ ነው” ብለዋል የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ኢራስቱስ ሙኤንቻ፡፡ ምክትል ሊቀመንበሩ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል “ከእርሳቸው የተሻለ ወዳጅ ሊኖረን አይችልም” ብለዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ "በምርመራ ወቅት ከባድ የማሰቃየት ድርጊት ተፋጽሞብናል" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል፤ ፍርድ ቤቱም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበርና የመድረክ አመራር አባል ዶ/ር መረራ ጉዲና የታሰሩት ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት ማድረግን በሚከለክለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።
የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ ዜና እረፍት ከተሰማ ጥቂት ቀናት ተቆጥረዋል።
የሠማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው የዮናታን ተስፋዬ ምስክሮች ሣይሰሙ ቀርተዋል፡፡
ለድርቅ ተጋላጭ በሆነችዋ ኢትዮጵያ ትኩረት ሊሠጠው የሚገባው ሥራ ለአደጋ የማይበገር ህብረተሠብን መፍጠርን እንደሆነ የብሔራዊ አደጋ ቅነሳ ሥራ አመራር ኮሚሽነር አስታወቁ፡፡
በደቡብ ምሥራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ በስድሣ ቀበሌዎች ውስጥ አስቸኳይ የውኃ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያውያን ዲምክራስያዊ ፓርቲ/ኢዴፓ/ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አንድ ጠንካር ተቃዋሚ ፓርቲ በመፍጠር በማጠናቀቅ ጥሪ አቀረበ።
ኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በሚሞቱ ሰዎች ብዛት በዓለም ቀዳሚ መሆኗ ተነገረ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ጋር መሠረታዊ በሆኑ ፖለቲካዊ ችግሮች ላይ ለመነጋገር መወያየታቸው ተነገረ፤ እስካሁን ግን ከገዢው ግንባር ተጨባጭ እርምጃ እንዳልተወሰደ የመድረክ መሪ አስታውቀዋል።
አቃቢ ሕግ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሃያ ሁለት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትና ደጋፊዎች ላይ የመሠረተው ክስ በዝግ ችሎት እንዲካሄደ ያቀረበውን ጥያቄ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ አራተኛ ወንጀል ችሎት በሙሉ ድምፅ ውድቅ አደርጎታል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቃቤ ህግና በተለያዩ ፓርቲዎች አመራር አባላት በእነ አቶ ሃብታሙ አያሌው እንዲሁም በአቃቤ ህግና በኢንተርኔት አምደኞቹ በነሶልያና ሽመልስ መካከል ባለው ክርክር ላይ ውሳኔ ሳይሰጥ ቀረ።
አቶ በቀለ ገርባን ጭምሮ በሽብር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ሃያ ሁለት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትና ደጋፊዎች ጉዳይ በዝግ ችሎት እንዲታይ ፍርድቤቱ ጥየቀ።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅን ተከትሎ የታሠሩ አባላቱን እንዲፈቱ ለጠቅላይ እዙ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ቁጥራቸው አስራ አንድ ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች ከዐዋጅ በኋላ መያዛቸውን ጠቅላይ እዙ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
አቃቢ ሕግ እነ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሽብር ወንጀል ከከሰሣቸው ሃያ ሁለት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትና ደጋፊዎች መካከል አምስቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ፍርድ ቤት ተገደው የመጡና ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውም ተናገሩ፤ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ተሟልተው እንዲቀርቡ ትዛዝ ሰጥቶ ተለዋጭ ቀጠሮ ቆርጧል፡፡
ዛሬ ለፍፃሜ የበቃው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት ኢትዮጵያውያን ውጤቱን ያልተጠበቀ ነው ብለውታል፡፡ ያዘኑ፣ የተበሳጩ፣ ስጋት ያደረባቸው ሴት አስተያየት ሰጪዎችም አሉ፡፡
ሠማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች አንዳንድ የአመራር አባላትን ጨምሮ ከሠማኒያ በላይ አባሎቹና ደጋፊዎቹ መታሰራቸውን አስታወቀ፡፡
ብዙ የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የእናቶችንና የሕፃናት ሞት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ውጤት ማስገኘታቸውን አንድ ዓለምአቀፍ ጥናት አስታወቀ።
ተጨማሪ ይጫኑ