ከፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ምንም ዓይነት ፍትሃዊ ውሳኔ እንደማይጠብቁ አቶ በቀለ ገርባ መልስ ሰጡ፡፡
ጎንደር ውስጥ በአማራና ትግራይ ሕዝብ መካከል የተካሄደው ሁለተኛ ዙር የአንድነት ጉባዔ ከተወያየባቸውና "መፍትሔ ተሰጥቶባቸዋል" ከተባሉት መካከል የትግራይ ፀገዴና የአማራ ጠገዴ ወረዳዎች፣ እንዲሁም የወልቃይት ጉዳይ ይገኙባቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በነመብራቱ ጌታሁን ዶሴ የሽብር ክሥ ተመሥርቶባቸው ክርክር ላይ የሚገኙት የወልቃይት ሕዝብ አማራ ብሔርተኛነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ መሪዎች ጉዳያቸውን ከሚያዩት ዳኞች አንደኛው እንዲነሱላቸው ጠይቀዋል፡፡
የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሕፃናት መብታቸው እና ደሕንነታቸው ተጠብቆ፣ እንዲያድጉ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በኦሮምያ ክልል በባቱ ወይንም በዝዋይ ከተማ የወላይታ ተወላጆች ብሔር ተኮር ጥቃት ተፈፀመብን አሉ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለእነ አቶ ጉርሜሳ አያኖ እንዲመስክሩ የሰጠው ትዕዛዝ አፀና፡፡
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሕይወቱ ያለፈው የአቶ አርማዬ ዋቄ የአሟሟት ሁኔታ እንዲጣራላቸው፣ አባት አቶ ዋቄ ማሙ ለፍርድ ቤት አቤቱታቸውን አቀረቡ፡፡
መድረክ በኢትዮጵያ ላይ አንዣቧል ካለው አደጋ እና ጥፋት ሊታደጋት የሚችለውና ብቸኛው አማራጭም ሥር ነቀል የፖለቲካ ለውጥ ነው ሲል አሳሰበ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በሃያ ስድሥት ሰዎች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ መሰርቷል፡፡
የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ሦስተኛ ምድብ ችሎት የቀድሞውን የአንድነትና ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሽበሺንና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ዛሬ በነፃ አሰናበተ፡፡
በኔዜርላንድስ ዘ ጌግ ከተማ በቀድሞ የደርግ አባል መቶ አለቀ እሸቱ አለሙ ላይ የተያዘው የፍርድ ሂደት ለማን አለብኝ ባይ ጨካኞች ማስጠንቀቂያ ነው ሲሉ አንድ የዘመኑ የስቃይ ሰለባ ተናገሩ፡፡
እነ አቶ በቀለ ገርባ ለቆጠሯቸው ምስክሮች ፍርድ ቤቱ የመጥሪያ ትዛዝ እንዳልፃፈ ታወቀ፡፡ ተከሳሾች ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን በአለፈው ዓመት መጀመሪያ ላይ በተፈጠረው ብሄር ተኮር ግጭት ከ28 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ልዩ መግለጫ አስታወቀ፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዛሬም እንዳልተፈቱ ታወቀ፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በዋስ እንዲለቀቁ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ትናንት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ በመጠየቁ እሥረኛው ዛሬም ሳይለቀቁ ቀርተዋል።
ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች፣ የሰጧቸው መልሶች ከሀገሪቱ እውነታ ጋር የሚስማሙ አይደለም ሲሉ ቪኦኤ ያናገራቸው የሁለት ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ገለፁ፡፡
ሕዝብን ከሕዝብ የመለያየትና የተሳሳተ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ እና ኪራይ ሰብሳቢነት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ዋነኛ ምክንያቶች እንደነበሩ የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ተናገሩ፡፡
መንግስት ጣቱን ከጠበንጃ ቃታ ላይ አንስቶ ለሕዝቡ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ይስጥ ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ። ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግም ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ አሳሰበ።
ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ያቀረባቸው ጥያቄዎች በቂ ምላሽ እንዲያገኙ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ጠየቀ፡፡
በኢትዮጵያ ሠብዓዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተለዋወጡ እንደሆነ እና ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በድርቅ፣ በጎርፍና በማኅበረሠቦች መካከል በሚፈጠረው ግጭቶች የተነሳ ፈተና እንደገጠማት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይንም ኦቻ አስታወቀ፡፡
በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ የሚመሰክሩ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለተከሳሽ እንዳይደርስ የፌደሬሽን ምክር ቤት ወሰነ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ