አዲስ አበባ —
የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሕፃናት መብታቸው እና ደሕንነታቸው ተጠብቆ፣ እንዲያድጉ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ዛሬ በተከበረው የዓለም የሕፃናት ቀን ላይ፣ ሕፃናት ችግሮቻቸውን ለመፍታት የተለያየ ዘዴዎችን መጠቀም እንደሚቻል አስረዱ፡፡
ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የሥልሳ አምስት ዓመት ቆይታም፣ ተወስቷል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ ማዕከል ነበር፣ የዓለም የሕፃናት ቀን ዛሬ የተከበረው፣ የበዓሉን ሥነስርዓት መድረክ ከማስተናበር አንስቶ አብዛኛውን ክንውን የመሩት ሕፃናት ናቸው፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ