አዲስ አበባ —
መንግስት ጣቱን ከጠበንጃ ቃታ ላይ አንስቶ ለሕዝቡ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ይስጥ ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ። ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግም ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ አሳሰበ።
ፓርቲው በመጭው ዕሁድ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሕዝብ ጋር እመክራለሁ ሲልም የአዳራሻ ውስጥ ስብሰባ ማዘጋጀቱንም አስታወቀ።
ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ከቀትር በኋላ በጠራው ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ ያሰራጨው የጽሑፍ መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አምባገነናዊ ሥርዓቱ ስለአንገሸገሸው ሥርዓቱን ለማውገዝና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለማስከበር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአደባባይ ተቃውሞ እያሰማ እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ