ጎንደር ውስጥ በአማራና ትግራይ ሕዝብ መካከል የተካሄደው ሁለተኛ ዙር የአንድነት ጉባዔ ከተወያየባቸውና “መፍትሔ ተሰጥቶባቸዋል” ከተባሉት መካከል የትግራይ ፀገዴና የአማራ ጠገዴ ወረዳዎች፣ እንዲሁም የወልቃይት ጉዳይ ይገኙባቸዋል።
በዚህ ዙሪያ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው ከአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ከአቶ ንጉሡ ጥላሁን ጋር ያደረገውን ውይይት በትናንቱ ሥርጭታችን አሰምተናል።
ፕሮግራማችንን የተከታተሉት የወልቃይት ሕዝብ አማራ ብሔርተኛነት የማንነት ጥያቄ ሊቀ መንበር አቶ በሪሁን ጥሩ የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከተናገሩት ጋር የማልስማማባቸው ጉዳዮች አሉ ስላሉ ጋብዘናቸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በነመብራቱ ጌታሁን ዶሴ የሽብር ክሥ ተመሥርቶባቸው ክርክር ላይ የሚገኙት የወልቃይት ሕዝብ አማራ ብሔርተኛነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ መሪዎች ጉዳያቸውን ከሚያዩት ዳኞች አንደኛው እንዲነሱላቸው ጠይቀዋል፡፡
አቤቱታቸውን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ አዝዞ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ