አዲስ አበባ —
በኦሮምያ ክልል በባቱ ወይንም በዝዋይ ከተማ የወላይታ ተወላጆች ብሔር ተኮር ጥቃት ተፈፀመብን አሉ፡፡ አያሌ የወላይታ ተዋላጆችም ከተማዋን ጥለው እየወጡ መሆናቸው ተነገረ፡፡
አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ግጭቱ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ለሕዝብን ግንኙነት ለማደፍረስ ባለሙ ጥቂት ሰዎች እንደሆነ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ አሁን ሁኔታው እንደተረጋጋም ይናገራሉ፡፡
በሁሉም ወገን ጥያቄ ያልተነሳበት ነጥብ የግጭቱ መንስዔ፣ ወይንም በባቱ ከተማ የወላይታ ተዋላጆች ላይ ለደረሰው ጥቃት መነሻ የሁለት ግለሰቦች ጠብ ነው ይባላል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ