አቶ ጉርሜሳ አያኖን ጨምሮ የአራቱ የኦፌኮ አመራር አባላት እና ሌሎች ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡
ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አንዱ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ያወጣውን መግለጫ አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አውንታዊ በሆነ መልኩ እንደተቀበሉት ይናገራሉ፡፡
በኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው ማረሚያ ቤት የሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አራት አባላት ዛሬ የይግባኝ ክርክራቸውን ሳያሰሙ ቀሩ።
ሰሞኑን በቢሾፍቱ ወይም ደብረ ዘይት ከተማ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሳቢያ፣ በአየር ኃይል ግቢ፣ ከ2ሽህ በላይ ወጣቶች ተጠግተው እንዳሉ ታወቀ።
በእሥር የሚገኙት አራቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት እነ ጉርሜሳ አያኖ ችሎት በመዳፈር ወንጀል ዛሬም ተጫማሪ የእሥር ቅጣት ተጣለባቸው፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዛሬው ዕለት አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን የንግድና ምጣኔ ኃብት ትስስር የተመለከተ ውይይት ተካሂዷል።
ኢህአዴግ በሚከተለው አክራሪ ኮሚኒስታዊ ቆኖና ምክንያት ለሀገሪቱ ችግሮች መፍትሄ መስጠት እንደማይቻለው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አስታወቀ፡፡
በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እንደገና እየታየ የሚገኘው ሁለቱ የኢንተርኔት አምደኞች፣ ዛሬ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ሳያቀርቡ ቀሩ።
ወልድያ ከተማ የመንግሥት ታጣቂዎች ፈፅመውታል ያሉትን የግፍ ግድያ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ አውግዘውታል።
በአማራ ክልል ወልድያ ከተማ ሲካሄድ በነበረው ሀይማኖታዊ ክብረ በዓል በተፈጠረ ግጭት ሰባት ሰዎች እንደተገደሉ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች እንደቆሰሉ ተገለፀ፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ/ኦፌኮ/ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የብሔራዊ መግባባቱን ሥራ በሙሉ ልብ እንዲያከናውን እና ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር በመሆን ለኢትዮጵያ እንደገና አዲስ ዘመን እንዲጀመር ጥሪ አቀረቡ፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ /ኦፌኮ/ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና የተመሰረተባቸው ክስ ተቋርጦ ዛሬ መፈታታቸው ታወቀ፡፡ አያሌ ደጋፊዎቻቸው እና የኦፌኮ አባላት በቤታቸው አካባቢ በአጀብ ተቀብለዋቸዋል፡፡
ኢህአዴግ እሥረኞችን ለመፍታትና ማዕከላዊን ለመዝጋት በወሰደው አቋም ወላዋይነትን አሳይቷል ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/እና ሰማያዊ ፓርቲ ነቅፈዋል።
ከነገ በስተያ ከሚለቀቁት መካከል ከአንድ ዓመት በላይ እሥር ቤት የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ይገኙበታል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት እነ ጉርሜሳ አያኖ በምስክርነት የቆጠሯቸው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዳይቀርቡ ወሰነ።
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በደራሼ ወረዳ የአመራር አባሎቹ የድርጅቱን ልሣን ጋዜጣ በማሰራጨታቸው እና በመሸጣቸው ምክንያት መታሰራቸውን፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አስታወቀ፡፡
መንግሥት ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ለዲሞክራሲ መስፈን ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እንዲያሳይ ሰመጉ ጠየቀ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በእሥር የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት እነ አቶ ጉርሜሳ አያኖ በምክርነት በቆጠሩዋቸው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አቀራረብ ላይ ውሳኔ እንዳልደረሰለት አስታወቀ፡፡
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ /ኦፌኮ/ ሊቀመንበር በዶ/ር መረራ ጉዲና እና በዓቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ