ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአሁኑ ወቅት በእሥር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እሥረኞች እንደሚፈቱና በዓቃቢ ሕግ የተመሰረተባቸው ክስም እንደሚቋረጥ ገለፁ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በእነ ጉርሜሳ አያኖ ጉዳይ በሚመሰክሩበት አግባብ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ቆርጧል፣ ሌሎች ተለዋጭ ቀጠሮዎችንም ሰጥቷል፡፡
"እነ ጉርሜሳ አያኖ" በሚል የክስ መዝገብ በእሥር ሆነው እየተከራከሩ የሚገኙት አራቱ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት፣ በምስክርነት የቆጠሯቸው ከፍተኛ የመንግሥቱ ባለሥልጣናት፣ ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።
የፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በኦሮሞ ፌዳራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ሊቀ መንበር በዶ/ር መረር ጉዲና ላይ አሥር ሲዲ ተጨማሪ ማስረጃ ማቀረቡ ተሰማ። የተከሳሹ ጠበቃ ተቃውሞአቸውን ለፍርድ ቤት ማቅረባቸውን ይናገራሉ።
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአለፈው ዓመት በድርጅቱ የተጀመረውን “በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ አፈፃፀም” የሚለውን በዝርዝር መገምገም መጀመሩን በመጥቀስ ማምሻውን መግለጫ አውጥቷል፡፡
የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አሁን በሀጋሪቱ እየታየ ነው ያለው ዘር ተኮር ግድያ እንዲቆም፣ ጠየቀ፡፡
በፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና በእነ ተሾመ ረጋሳ መካከል ባለው የሽብር ክስ ክርክር ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ብይን ሰጠ፡፡
"የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሰላም ተነሳሽነት" በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀስ አካል በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን፣ ሰላም ያለመኖር ሁኔታን ለመቀየር መነሳቱን አስታውቋል፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ /ኦፌኮ/ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ለዋስ መብታቸው መታገድ የሰጡት መልስ "ተገቢ ያልሆነና ሕግን ያልተከተለ ነው" ሲል ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መልስ ሰጠ፡፡ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአቶ በቀለ ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ እንዲያፀናም ጠይቋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ለሀገር ችግሮች መፍትኄ አፋላላጊ መሆኑን ገለፀ።
"ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ የሰብአዊ መብቶች አያይዝ እያሽቆለቆለ በመሄዱ ምክንያት የተፈጠሩ ችግሮች ለሀገሪቱ ደኅንነትና ህልውናም ጭምር አስጊ ደረጃ ላይ ደርሰዋል" ሲል ሰመጉ አስታውቋል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስድሥተኛ ፍትሐብሔር ችሎት የፍርድ ባለመብቶች በሆኑ ዘጠና ሥምንት ሰዎችና በዙና ትሬዲንግ መካከል ባለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ቆርጧል፡፡
ዛሬ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ ከተማ ሰመራ ላይ በተከበረው አሥራ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ጠ/ሚኒስትሩ በቅርቡ በተከሰቱ ግጭቶች የጥፋት ኃይሎችና ኮንትሮባዲስቶች ያሏቸውን ከሰሱ፡፡
አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በሚቀጥሉት አሥራ ሁለት ዓመታት ወደ 1መቶ 38 ሚሊዮን እንደሚደርስ ተገመተ፡፡
በአንድ ሀገር የሚተከል የአስተዳደር ዓይነት ለውጥን፣ ልማትንና ዲሞክራሲያዊ ግንባታን የሚያብራራ እና የሚገፋ ኃይል እንደሆነ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡
አቃቤ ሕግ ዛሬ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ የቆጠራቸው ሁለት ተጨማሪ ምስክሮች ፓሊስ ሊያቀርባቸው እንዳልቻለ ገለፀ፡፡
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ አንዳንድ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ብሄር ተኮር ወከባና ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተናገሩ፡፡
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎበት የነበረው የሽብር ወንጀል ተሽሮ በመደበኛ ወንጀል ድንጋጌ ተፈረደበት።
በዝቅተኛው የልማት እርከን ላይ የሚገኙት የዓለም ታዳጊ ሀገሮች፣ የኃይል አቅርቦትን ለቤትና ለምርት ለአገልግሎት በማዳረስ ረገድ በእጅጉ ወደ ኋላ እየቀሩ መሆናቸውን አንድ የመንግሥታቱ ድርጅት ዘገባ አስታወቀ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ