ዋሺንግተን ዲሲ/አዲስ አበባ —
በአማራ ክልል ወልድያ ከተማ ሲካሄድ በነበረው ሀይማኖታዊ ክብረ በዓል በተፈጠረ ግጭት ሰባት ሰዎች እንደተገደሉ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች እንደቆሰሉ ተገለፀ፡፡
የክልሉ ፕሬዚዳንት ሁኔታውን ለማረጋጋት በስፍራው እንደሚገኙ ተነገረ፡፡ እጥፊዎች ማንነታቸው ተለይቶ በሕግ እንዲጠየቁም ከህዝብ የቀረበውን ጥያቄ ፕሬዚዳንቱ ተቀበሉ፡፡
በሌላ በኩል ቪኦኤ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪ በሰጡት የዓይን እማኝነት የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሆኑ ወታደሮች ታቦት ይሸኝ በነበረ ሰው ላይ አስለቃሽ ጋዝ መርጨታቸውን እና ተኩስ ከፍተው ሰላማዊ ሰው መግደላቸውን ገልፀዋል፡፡
እኝሁ እማኝ አክለውም በከተማይቱ ውስጥ ከአንድ ወር በበለጠ ጊዜ ጎሳ ተኮር ውጥረት ሰፍኖ መቆየቱን አመልከተው፣ የመንግሥቱ ባለሥልጣናት ሁኔታውን ለማርገብ የሚያስችል ምንም እርምጃ ሳይወስዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ