አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ —
ከነገ በስተያ ከሚለቀቁት መካከል ከአንድ ዓመት በላይ እሥር ቤት የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ይገኙበታል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ዓመታት በተፈጠረው ሁከት ውስጥ ተሣትፈዋል ያሏቸው 528 ተጠርጣሪዎች ክሥ ተቋርጦ ከነገ በስተያ ረቡዕ፤ ጥር 9/2010 ዓ.ም. እንደሚፈቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጌታቸው አምባዬ አስታውቀዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ወራት በሚካሄድ ምርመራ ሌሎችም እሥረኞች እንደሚለቀቁ ተገልጿል።
በዚህኛው የመጀመሪያ ዙር የተፈረደባቸው ሰዎች እንደማይፈቱ ተጠቁሟል።
ፌደራል ክሥ ከተመሠረተባቸው 115 እሥረኞች ሌላ 361 በደቡብ ክልል ዲላ ዙሪያ ወረዳ ይርጋጨፌ፣ ኮቸሬና ገደብ 361፣ በኮንሶ ወረዳ 52 ሰዎች እንደሚፈቱ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ አመልክተዋል።
“እሥረኞቹ ከመለቀቃቸው በፊት የሁለት ቀናት የተሃድሶ ትምህርት ይሰጣቸዋል” ተብሏል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ