አዲስ አበባ —
በኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው ማረሚያ ቤት የሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አራት አባላት ዛሬ የይግባኝ ክርክራቸውን ሳያሰሙ ቀሩ።
ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱ ደንበኞቻቸውን እንደሚጠቅም የአቤት ባይ ጠበቆች ተናግረዋል። ክርክራቸውን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ለማሰማት ለሦስት ዓመት ያህል የጠበቁት አራቱ የሙስሊሙ ማህበረሰርብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ዛሬም ክርክራቸውን ለማቅረብ አልቻሉም፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ