አንዳንድ የአፍሪካ ሃገሮች የኮሮናቫይረስን መተላለፍና መስፋፋት ለመቆጣጠር በሚል ያወጧቸውን ገደቦችና ድንጋጌዎች ለማስፈፀም ወታደሮቻቸውን ማሰማራታቸው በብዙዎች ዘንድ ሥጋትን አሳድሯል። ሥጋቱ በተለይ ግጭቶች በተለመዱባቸው አካባቢዎች ይበልጥ ማየሉ እየተነገረ ነው።
በኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ለማንሳት በዚያች ሃገር ተጨባጭ ለውጦች መካሄድ ይኖርባቸዋል ሲሉ አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት አስገንዝበዋል።
በምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ሃገር እየተካሄዱ ያሉ ከዚህ ቀደም ታይተው ያልታወቁ ለውጦችን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ ጋር ያሏትን ግንኙነቶች ማጠናከር አለባት ሲሉ አንድ ከፍተኛ አሜሪካዊ ዲፕሎማት አስገነዘቡ።
የትነበርሽ ንጉሤ የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋች የ2018 ሔለን ኬለር ኢንተርናሽናል ተሸላሚ ከኒውዮርክ ስቱዱዮችን ስለ ሽልማት ሥነ ስርዓቱ፣ ስለ ሕይወት ተሞክሮዋ ከጋዜጠኛ ሳሌም ሰለሞን አጭር ቆይታ አድርጋለች፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሀገሮቻቸው እንዲመለሱ ያዘዘቻቸውን ዜጎቻቸውን ለማይቀበሉት አራት ሃገሮች ዜጎች ቪዛ መስጠት ለማቆም ማቀድዋ ታውቋል።
ከኤርትራ ጋር ግንኙነት ፈጥሮ አሸባሪነትን ለመዋጋት አጋርነትን መፍጠር የሚያስፈልግበት ጊዜ ደርሷል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ሪፓብሊካን አባል ተናገረዋል፡፡
በቀድሞ ታሣሪዎችና የየመን ባለሥልጣናት መግለጫ መሠረት የተባበረው የአረብ ራቢጣ ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ከየመን ወደ አሰብ ኤርትራ ድብቅ እሥር ቤት አዛውራለች።
ካታር ሰላም አስከባሪዎቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ኤርትራ በጋራ ድንበራችን ላይ ያለውን አጨቃጫቂ ግዛት ወርራ ተቆጣጥራለች ስትል ጅቡቲ ከሰሰች።
ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ ባሕር ኃይል ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለች፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ተላላፊ ሶማሌ ክልል መግባቱን አስታውቋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ምንም እንኳ ዓለምቀፍ ማዕቀብ ቢጣልባትና እንድትገለል ቢደረግም፣ የጦር መሣሪያ ለመግዛትና የጋራ መከላከያ ስምምነት ለመፈራረም፣ ፍላጎት ያላቸው በርካታ የአፍሪካ ሀገሮችን ሽርክና ማግኘት ችላለች ይላል፤ ምርመራውን ያካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ባለሞያዎች ቡድን።
ባለፈው ዓርብ አንዲት ኒስሪን ኤላሚን የተሰኘች በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ለዶክትሬት ዲግሪ የምትማር ሱዳናዊት በሃገሯ ጥናት ስታካሂድ ቆይታ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመመለስ ላይ ነበረች።
በኢትዮጵያ የኦሮምያ ክልል ሲካሄድ በቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት የውጭ ሀገር ዜጎች ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ድርጊቱ የሀገሪቱን የምጣኔ ሃብት ዕድገት ሊያሰናክል ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። ተንታኞች ግን የምጣኔ ሃብት ዕድገቱ እንዲቀጥል አንዱ ቁልፍ ርምጃ የተቃዋሚዎችን ብሶት አድምጦ መፍትሄ መስጠት መሆኑን ይመክራሉ።
ኢትዮጵያ ባለፈው ሣምንት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት መመረጧን ተከትሎ ከተለያዩ ወገኖች የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው፡፡ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋች ድምፃቸውን ቀድመው ካሰሙት ወገኖች መካከል ሆኖ ይገኛል፡፡
አንድ የእሥራኤል ፍርድ ቤት፣ ባለፈው ጥቅምት ወር በደቡባዊ እሥራኤል በርሸባ ከተማ በሚገኝ አውቶቡስ ጣቢያ አካባቢ በአንድ ኤርትራዊ ስደተኛ ላይ ግድያ ከፈጸሙ ቡድኖች ጋር ተባባሪ ነው የተባለውን የእስር ቤት ሠራተኛ በነፃ መልቀቁ ተነገረ። ኤርትራዊው ሀብቶም ዘርኦም የተገደለው ከሌላ ነፍሰ-ገዳይ ጋር በተምታታ የማንነት ጥያቄ ምክንያት መሆኑንም ዘገባው ይገልጻል።
ተጨማሪ ይጫኑ