በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረብ ራቢጣ የሽብር ተጠርጣሪዎችን ወደ ኤርትራ እሥር ቤት ይልካል ተባለ

በቀድሞ ታሣሪዎችና የየመን ባለሥልጣናት መግለጫ መሠረት የተባበረው የአረብ ራቢጣ ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ከየመን ወደ አሰብ ኤርትራ ድብቅ እሥር ቤት አዛውራለች።

በቀድሞ ታሣሪዎችና የየመን ባለሥልጣናት መግለጫ መሠረት የተባበረው የአረብ ራቢጣ ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ከየመን ወደ አሰብ ኤርትራ ድብቅ እሥር ቤት አዛውራለች።

በቀይ ባህር ጠረፍ ላይ የሚገኘው ሚስጥራዊ እሥር ቤት ሰቆቃና ግፍ በብዛት ይፈጸምባቸዋል ከሚባሉ በአካባቢው ከተቋቋሙ በርካታ የእሥር ቤቶች መረብ አንደኛው መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪልና ሂዩማን ራይትስ ዋች ያካሄዱት ምርመራ አጋልጧል።

በሂዩማን ራየትስ ዋች ጥናቱን ያደረጉት ክርስቲን ቤከርሊ እንዳስረዱት የተባበረው የአረብ ራቢጣና የየመን ሸሪኮቹ ታሣሪዎቹን የሚመለከቷቸው በየመን የአልቃይዳ አሸባሪዎችን እየተዋጋች ያለችውን የአረብ ራቢጣ ጥረቶች ለማክሸፍ እንደሚንቀሳቀሱ ከባድ የሽብር ወንጀለኞች አድርገው ነው።

የሂዩማን ራይትስ ዋች ተመራማሪዎች በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ በእሥረኞች ላይ የሚፈፀመውን የመብት ጥሰት ለመመዝገብ የመንን ጎብኝተዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአረብ ራቢጣ የሽብር ተጠርጣሪዎችን ወደ ኤርትራ እሥር ቤት ይልካል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG