በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኅዳሴ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ውሎ


እንደራሴ ኬረን ባስ
እንደራሴ ኬረን ባስ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ትናንት ከሰዓት በኋላ ተነጋግሯል።

ለስብሰባው ጠለቅ ያለ ማብራሪያ የሰጡት የመንግሥታቱ ድርጅት የፖለቲካና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝሜሪ ዲካርሎ የኅዳሴ ግድብ ሥራ ከተጀመረ አንስቶ ያለውን ታሪክና ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን እንዲሁም መሪዎቻቸው የተጓዙባቸውን መንገዶች ጠቋቁመዋል።

ሰሞኑንም የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር በሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፖሳ ሰብሳቢነት በተጠራ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ኤል ሲሲና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላ ሃምዶክ በተገኙበት ስብሰባ ላይ መሪዎቹ ቀሪ ጉዳዮቻቸውን ለመፍታት በአፍሪካ ኅብረት ወደሚመራ ሂደት ለመግባት መስማማታቸውን ረዳይ ዋና ፀሐፊዋ ዲካርሎ ለፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ አሳውቀዋል።

በሦስቱ ሃገሮች መካከል በሚካሄዱት ድርድሮች የቀሩት በተፈጥሯቸው የቴክኒክና የሕግ ጉዳዮች መሆናቸውን ዲካርሎ ጠቁመው እነዚህም የሚደርሱበት ስምምነት አሳሪነት፣ የውዝግብ አፈታት ሥርዓትና በድርቅ ጊዜ የውኃ አያያዝን እንደሚያካትቱ ተናግረዋል።

ረዳት ዋና ፀሐፊዋ አክለውም ወገኖቹ ስምምነት ላይ ለመድረስ ቁርጠኛ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበው የአፍሪካ ኅብረት ሂደቱን እስከፍፃሜው ለመምራት እያደረገ ያለውን ጥረትም አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅም ለጋራ ተጠቃሚነት የሚያደርሳቸውን ጥረት ጠብቀውና አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን መተማመን አጉልተው ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ሰሞኑን መግለጫ ያወጣው የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የጥቁር እንደራሴዎች ጉባዔ በግድቡ አሞላልና በሌሎችም የቴክኒክ ጉዳዮች የተነሣው ውዝግብ በሰላምና በመግባባት እንዲፈታ ለማስቻል ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቆ ጉዳዩን አህጉራዊው የአፍሪካ ኅብረት እንዲይዘው እንደሚያበረታታም ገልፆ ነበር።

የኅዳሴ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:38 0:00

በጉባዔው መግለጫ ላይ ከቪኦኤ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሊቀመንበሯ የካሊፎርኒያ እንደራሴ ኬረን ባስ የደብዳቤአቸው ዋና ሃሳብና የእርሳቸውም አመለካከት ሦስቱ ሃገሮች ለችግሮቻቸው መፍትኄውን እራሳቸው እንዲፈልጉ መሆኑን ተናግረዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከሦስቱም ሃገሮች ከእያንዳንዳቸው ጋር ያሏት ግንኙነቶች የተለያዩ በመሆናቸው በጉዳዩ ውስጥ መግባቷ አሳስቧቸው እንደነበርም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በዳያስፖራ ያሉ አሥራ አምስት የኢትዮጵያዊያን ሲቪክ ማኅበራት በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ሰሞኑን መግለጫ አውጥተዋል።

የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ባለሙያዎች፣ ምሁራንና የመብቶች ተሟጋቾች በዚሁ መግለጫቸው ለኢትዮጵያ መንግሥት ጥረቶች ያላቸውን ድጋፍና አድናቆት ከመግለፅም አልፈው ሌሎችም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ማንኛቸውንም ልዩነቶቻቸውን አስወግደው ከመንግሥቱ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አሰምተዋል። ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ባለስድስት ነጥብ ጥያቄ አቅርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኅዳሴ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:46 0:00


XS
SM
MD
LG