ዋሺንግተን ዲሲ —
አንዳንድ የአፍሪካ ሃገሮች የኮሮናቫይረስን መተላለፍና መስፋፋት ለመቆጣጠር በሚል ያወጧቸውን ገደቦችና ድንጋጌዎች ለማስፈፀም ወታደሮቻቸውን ማሰማራታቸው በብዙዎች ዘንድ ሥጋትን አሳድሯል።
ሥጋቱ በተለይ ግጭቶች በተለመዱባቸው አካባቢዎች ይበልጥ ማየሉ እየተነገረ ነው።