ማክሰኞለት የተባበሩት መንግስታት የመብት አጣሪ ቡድን የኤርትራ ባለስልጣናት በዜጎቻቸው ላይ እየፈጸሙ ነው ያላቸውን ሰፊ የመብት ጥሰቶች፤ አስረድቶ የኤርትራ መሪዎች በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወይንም በሌሎች የፍትህ ችሎቶች ክስ እንዲመሰረትባቸው መጠየቁ ይታወሳል።
የዛሬውን የአፍሪካን ቀን ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን ዛሬ ባወጡት መግለጫ፤ ሰብአዊ መብትን ሙሉ በሙሉ ማስከበር የአፍሪካ ህብረት 2063 አጀንዳ ነው ብለዋል።
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሀገራቸው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተጣለባት ማእቀብ ሳያግዳት ፈጣን ልማት እያስመዘገበች ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ጉባዔ በዛሬው ዕለት በቱርክ ኢስታንቡል ተከፍቷል። የረድኤት ተቋማት መሪዎችና መንግሥታት በተወከሉበት በኢስታንቡሉ ጉባዔ የተገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ በተሰጠው ምላሽ የተሻሉ የተባሉትን አሠራሮች በተመለከተ ለመድረኩ አቅርበዋል።
አቶ ምትኩ በድርቅ በተመታች ሃገር ቅስፈታዊ የጎርፍ አደጋ የተከሰተበትን ምክንያት አብራርተዋል። ፖል ሃንድሊ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች የኦቻ ክፍል ሃላፊንም ለጎርፍ አደጋ አስቸኳይ ምላሽ የሚደረገውን ጥረት አብራርተውልናል።
የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ በአዲስ አበባ የባህልና የፈጠራ ማዕከል ከፈተ።
የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀን በዛሬውለት ሲከበር፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ ምንም እንኳን የጋዜጠኞች ይዞታቸው ቢለያይም “አፋኝ” መንግስታት መሆናቸው ነው የተስተጋባው። የአለም የመገናኛ ብሀን ነጻነት ቀን ከመከበሩ አስቀድሞ የጋዜጠኞች ይዞታና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ሁኔታ የሚያሳስባቸው የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የተለያዩ ዘገባዎችን አውጥተዋል።
በዓለም ዙሪያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት አሽቆልቁሏል፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ “አፋኞች” ተብለዋል በዛሬውለት ይፋ በሆነ ዓመታዊ ጥናት። በዋሽንግተን ዲሲ መሰረቱን ያደረገው የመብት ተሟጋች ቡድን ፍሪደም ሀውስ በዓለም ዙሪያ ከሰባት ሰዎች መካከል ስድስቱ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ባልተጠበቀባቸውና የጋዜጠኞች ደህንነት ዋስትና በሌለባቸው ሀገሮች ይኖራሉ።
በሜዲትራንያን ባህር ከደረሰ የጀልባ አደጋ የተረፉ ኢትዮጵያዊና ሶማሊያዊ ወጣቶች ትናንት ግሪክ ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በባህር ላይ ሰዎች ሰምጠው ሲሞቱ እንዳዩ ተናግረዋል።
በሜዲትራንያን ባህር ከደረሰ የጀልባ አደጋ የተረፉ ኢትዮጵያዊና ሶማሊያዊ ወጣቶች ትናንት ግሪክ ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በባህር ላይ ሰዎች ሰምጠው ሲሞቱ እንዳዩ ተናግረዋል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) እሮብ በህይወት ከተረፉት ሰዎች ባገኘው መረጃ መሰረት የሞቱት ሰዎች 500 ሊደርሱ እንደሚችሉ ያደረበትን ስጋት ገልጿል።
በድርቁ በተጠቁ ሌሎች አካባቢዎችም ወደ ሰማንያ ከመቶ የሚሆኑ የቤት እንስሳት መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የእርዳታ ሰራተኞች አስታውቋል። በአፋር ኤሊዳርና ገዋኔ ወረዳዎች ከብቶች በግጦሽና ውኃ እጥረት ሞተዋል፤ የተረፉት ደግሞ ሰውነታቸው መንምኖና በበሽታ ተጠቅተው ይታያሉ።
በድርቁ ምክኒያት ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ለተረጂነት ተጋልጠዋል። የተባበሩት መንሥታት ድርጅት የ 90 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል።
ኤርትራ ላለፉት ስምንት ዓመታት ይዛቸው የቆየቻቸውን አራት ጂቡቲያዊያን የጦር እሥረኞችን ለቅቃለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የጦር እሥረኞቹን መፈታት ዜና በአድናቆት መቀበላቸውን አስታውቀዋል። የቀሪዎቹ እሥረኞች ደኅንነት እንደሚያሰጋት ግን አሜሪካ ገልፃለች።
ሁለት የዓለምአቀፍ ጋዜጠኞች እና አስተርጓሚያቸው በኦሮሚያ ተቃውሞና ድርቅ ዙሪያ ዘገባ ለማቅረብ በተንቀሳቀሱበት ወቅት፤ በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ተመለሱ። ጋዜጠኞቹ ለ24 ሰዓታት ታስረው ተለቀዋል።
በኢትዮጵያ ከተሞች በተለይም በመዲናችን በአዲስ አበባ አንድ የተለመደ ግን ትክክል ያልሆነ ልምድ አለ። ሰውን ያለአግባብ በቃላት መዝለፍ፣ መስደብ ከዛም ባለፈ የሰውነት ትንኮሳ፤ በተለይ በሴቶች ላይ።
ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው የዓለምን ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ የፈተሸ ዘገባ የአሮፓዊያኑ 2015 ዓ.ም. የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ማሽቆልቆሉን ገልጿል። በተለይ በአፍሪካ ቀንድ - በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሰብአዊ መብቶች በብርቱ የተጣሱበት ዓመት እንደነበረ ድርጅቱ ጠቅሷል።
"መንግሥት የሚወስዳቸው የኃይል እርጃዎች ወደ አፍሪቃ ቀንድ ዘምተው እስከ ኢትዮጵያና ኤርትራ ተዳርሰዋል።" ሚሸል ካጋሪ በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት የምስራቅ አፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ቀንድና የግሬት ሌክስ አገሮች ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር
ከሕዳር ወር 2008 ዓም ጀምሮ በሰፋት በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደዉን ተቃዉሞ የኢትዮጵያ ጸጥታ ሃይሎች በጉልበት እያፈኑት ነዉ ይላል ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች (Human Rights Watach) ዛሬ ባወጣዉ ዘገባ።
ምዕራብ አርሲ ውስጥም ከከትናንት በስተያ አንስቶ ግጭቶች መኖራቸው ተሰምቷል።
ፕረዚደንት ኦባማ ንግግራቸውን ከመጀመራቸው በፊት የ19 ዓመቷ ሰባህ ሙክታር ንግግር አቅርባ ነበር።
ተጨማሪ ይጫኑ