በድሬደዋ ከተማ በወጣቶች መካከል የሚነሳ ተደጋጋሚ ግጭት ለሞት እና ንብረት መቃጠል ምክኒያት እንደሆነ ነዋሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የከተማው አስተዳደርና ፖሊስ ገለፁ።
ወ/ሮ መአዛ በፍርድ ቤቶች ዙሪያ ያሉትን ችግሮች እንደሚረዱና ይህንን ለማሻሻልም ጠንክረው እንደሚሰሩ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ ማንም ተነስቶ እንደፈለገው የሚጋግራት የግል ርስት ሳትሆን ዘመናትን ያስቆጠረች ታላቅ ሕዝብ የመሠረታት አገር ነች" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ፍራንክፈርት-ጀርመን ላይ ለተሰበሰቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ባደረጉት ንግግር።
በአፍሪካ የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰት ላይ እየተነጋገረ ያለ ከፍተኛ ስብሰባ ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ውስጥ እየተካሄደ ነው።
ጀርመን ውስጥና በሌሎችም የአውሮፓ ሃገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ሲያካሂዱ የቆይዋቸውን የተቃውሞ ሰልፎች ከዚህ ለብዙ ዓመታት በማስተናገድ የሚታወቀው በርሊን ከተማ እምብርት ላይ የሚገኘው ብራንደንቡርግ ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የወጣ የድጋፍ ሰልፍ አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ታይቶበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ዛሬ በፈርንሳይ ጉዞ ጀምረዋል። ከነገ በስቲያም ፍራንክፈርት ውስጥ ከ20 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ዜጎችን ያገኛሉ ተብሏል። ስለ ዝግጅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም፣ በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር መርጋ በቃና እና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ኃይለሚካኤል አበራን አነጋግረናቸዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለዶክትሬት ማጠናቀቂያ ጥናታቸው ወደ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ወደ አዲስ አለም ከተማ ተጉዘው የነበሩ ግለሰቦች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሁለቱ ሲገደሉ አንዱ መቁሰሉን የዞኑ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ባዋቀሩት አዲስ የካቢኔ አባላት ውስጥ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ወ/ሮ አይሻ መሐመድ ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ የሚባል ዜጋ የለም "ኢትዮጵያ ለሁሉም እኩል የሆነች አገር ናት" ብለዋል። ይህ ደግሞ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋል እንደሌለበት ገልፀው፤ "ፖለቲከኛም፣ ጤነኛም ሆነ በሽተኛ መሆን የሚቻለው አገር ስትኖር ነው" ብለዋል።
ከትላንት በስቲያ የታሰሩት ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉና አቶ ሚካኤል መላከ ያለ ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።
ከአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተይዘው ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ተወስደው የነበሩ ወጣቶች መለቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ አስታውቋል።
ባለፈው ሳምንት ለደመወዝና ለጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ከነትጥቃቸው ወደ ቤተ-መንግሥት የሄዱት ወታደሮች “የለውጥ ሂደቱን የማደናቀፍ ዓላማ ባላቸው አካላት የተላኩ ነበሩ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልፀዋል።
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሚገኘው አማሮ ወረዳ ላይ በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነ የወረዳው አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገለፁ። ስለጉዳዩ መረጃ እንደደረሳቸው የተናገሩት የኦነግ ሥራ አስፈፃሚ አባልና ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ በበኩላቸው “ድርጊቱ የተፈፀመው ‘በኦነግ ሠራዊት ነው፤ አይደለም’ የሚለውን በማጣራት ላይ ነን” ብለዋል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ የስልጠና ቤት ገንብተው ሕገ ወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩት ወጣቶች “ከተማ ውስጥ ከተፈጠረው ግጭት ጋር ግንኙነት የላቸውም” ሲል የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
ዶ/ር አወል በማከል “በሕገመንግሥትና በሕግ በግልፅ እንደተቀመጠው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በሰላማዊ መንገድ ትግል ለማድረግ መርጦ ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ታጣቂዎች ሊኖሩት” አይገባም ብለዋል።
በሃዋሳ ከተማ ከትናንት በስቲያ መስከረም 29/2011 ዓ.ም ምሽት በተለምዶ አሮጌው ገበያ ተብሎ በሚጠራው ትልቁ የከተማው የገበያ ሥፍራ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ የነጋዴዎቹን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ማውደሙን ነዋሪዎች ገለፁ።
በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት ትጥቁን መፍታተ እንዳለበት የኢትዮጵያ መንግሥት አሳሰበ።
በየአራት ዓመቱ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት የአገራት የሰብዓዊ መብት መገማገሚያ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ለመገምገም የሚያስችል ሰነድ ቀረበ። ሰነዱን ካቀረቡት የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውስጥ፤ ሲቪከስ፣ሲፒጄ፣ዲፌንድ ዲፌንደርስ፣አርቲክል 19፣አክሰስናው፣ ፔን ኢንተርናሽናልና ኢመድህ ይገኙበታል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የመመለስ ሥራ እየተሠራ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የከማሽ ዞን ተፈናቃዮች በነቀምት ከተማ ሕዝብ ከሚደረግላቸው ድጋፍ ውጪ ከመንግሥት ያገኙት ዕርዳታ እንደሌለ ገልፀው፤ በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ከሁለቱ ክልል ባገኘነው አጠቃላይ መረጃ በከተማው ውስጥ ከተገደሉት ሰዎች ጭምር በአምስት ቀናት ውስጥ የ67 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ተጨማሪ ይጫኑ