በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ ጎጃም ዕጩ ሁለት ዶክተሮች ተደብድበው ተገደሉ


ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለዶክትሬት ማጠናቀቂያ ጥናታቸው ወደ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ወደ አዲስ አለም ከተማ ተጉዘው የነበሩ ግለሰቦች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሁለቱ ሲገደሉ አንዱ መቁሰሉን የዞኑ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

አጥኒዎቹ በከተማው ባለው አንድ ትምሕርት ቤት ውስጥ ለምርምር የሚሆን የሽንትና የዐይነ ምድር ናሙና እየሰበሰቡ ባሉበት ወቅት፤ “ሦስት ተማሪዎች ሞቱ” የሚል ወሬ በመሰራጨቱ ተቆጥተው በመጡ የአካባቢው ወጣቶች በደረሰባቸው ከፍተኛ ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ አንማው ዳኛቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ለቤተ ክርስቲያን ህንፃ ግንባታ ግልጋሎት የሚውል ሲሚንቶ በራሳቸው መኪና ጭነው ወደ አካባቢው ተጉዘው የነበሩ ጥንዶች ንብረትም መቃጠሉ ታውቋል። በዚህ ድርጊት ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩም 30 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግርዋል። በተፈፀመው ድርጊት የአካባቢው ማኅበረሰብም ሆነ መንግሥት ማዘኑን አቶ አንማው ገልፀው በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉትን ማሰር መቀጠሉን ጠቁመዋል።

(ከኃላፊው ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በምዕራብ ጎጃም ዕጩ ሁለት ዶክተሮች ተደብድበው ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:37 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG