በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠበቃ ሄኖክና አቶ ሚካኤል ያለ ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አምነስቲ ጠየቀ


ከትላንት በስቲያ የታሰሩት ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉና አቶ ሚካኤል መላከ ያለ ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ፖሊስ በምርመራ ጊዜ መጠየቂያ መዝገብ ላይ ለክሱ መነሻ አድርጎ ያቀረበው የመደራጀት ምክንያት “መብት” እንጂ “ወንጀል” አይደለም ሲሉ የአምነስቲ የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪ አቶ ፍሰሃ ተክሌ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሰባት ቀን ፈቅዷል።

ጠበቃ አለልኝ ምሕረቱ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ከፍልስጥዔም ኤምባሲ ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ መባሉ እንዳሣዘናቸው ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

ጠበቃ ሄኖክና አቶ ሚካኤል ያለ ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አምነስቲ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG