ዋሽንግተን ዲሲ —
ባለፈው ሳምንት ለደመወዝና ለጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ከነትጥቃቸው ወደ ቤተ-መንግሥት የሄዱት ወታደሮች “የለውጥ ሂደቱን የማደናቀፍ ዓላማ ባላቸው አካላት የተላኩ ነበሩ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልፀዋል።
የወታደሮቹ ሐሳብ ክፋት ይኑርበት አይኑረው ስላልታወቀም ብልሹ ሁኔታ ሳይፈጠር ሁኔታው በዘዴ መፈታቱን ተናግረዋል።
ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ካቢኔ ድረስ ያለው የተቋም ብቃት አነስተኛ መሆኑን በዛሬው ንግግራቸው የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ችግር የፈጠረን ጭንቅላት - ችግር ፈቺ ማድረግ ቀላል አይደለም” ብለዋል።
በሰሞኑ የፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ የፓርላማው የዘንድሮ ሥራ የመክፈቻ ንግግር ዙሪያ ከአባላቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ በሰጡበት በዛሬው ንግግራቸው ግድያዎችን፣ የዜጎች መፈናቀልን፣ የደሞዝ ጭማሪና የበጀት ምደባን አስመልክቶ ለተነሱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ)
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ