በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጦላይ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ተወስደው የነበሩ ወጣቶች መለቀቃቸውን ፖሊስ አስታወቀ


የአዲስ አበባ ወጣቶች በጦላይ
የአዲስ አበባ ወጣቶች በጦላይ

ከአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተይዘው ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ተወስደው የነበሩ ወጣቶች መለቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ አስታውቋል።

ዛሬ የተለቀቁት 1 ሺህ 174 ወጣቶቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ እንደነበረና የተሰጣቸውን ሥልጠና ማጠናቀቃቸውን ኮሚሽኑ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

ወጣቶቹ ዛሬ እንደሚፈቱ ቀደም ሲል ገልፆ የነበረው ፌደራል ፖሊስም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለተባለው ሥልጠና ወደ ጦላይ የተወሰዱት ወጣቶች ቁጥር 1 ሺህ 204 እንደሆነ አስታውቆ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ለፓርላማው በተናገሩበት ወቅት የእነዚህኑ ወጣቶች ጉዳይም አንስተው ነበር።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ጦላይ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ተወስደው የነበሩ ወጣቶች መለቀቃቸውን ፖሊስ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:23 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG