ዋሽንግተን ዲሲ —
በየትኛውም ደረጃ ያለ ማንኛውም የመንግሥት አመራር ላይ ያለ ሰው ገለልተኛ መሆን እንዳለበት የተናገሩት ወ/ሮ አይሻ፤ "ይህን ደግሞ በሚያንፀባርቁት ሐሳብም በድርጊትም ማሳየት ይገባቸዋል።"ብለዋል።
(የምሕንድስና ባለሞያዋ ወ/ሮ አይሻ መሐመድ ከአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ ጋር ያደረጉትን ሰፋ ያለ ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ። )
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ባዋቀሩት አዲስ የካቢኔ አባላት ውስጥ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ወ/ሮ አይሻ መሐመድ ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ የሚባል ዜጋ የለም "ኢትዮጵያ ለሁሉም እኩል የሆነች አገር ናት" ብለዋል። ይህ ደግሞ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋል እንደሌለበት ገልፀው፤ "ፖለቲከኛም፣ ጤነኛም ሆነ በሽተኛ መሆን የሚቻለው አገር ስትኖር ነው" ብለዋል።
በየትኛውም ደረጃ ያለ ማንኛውም የመንግሥት አመራር ላይ ያለ ሰው ገለልተኛ መሆን እንዳለበት የተናገሩት ወ/ሮ አይሻ፤ "ይህን ደግሞ በሚያንፀባርቁት ሐሳብም በድርጊትም ማሳየት ይገባቸዋል።"ብለዋል።
(የምሕንድስና ባለሞያዋ ወ/ሮ አይሻ መሐመድ ከአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ ጋር ያደረጉትን ሰፋ ያለ ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ። )
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ