በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ የሚገመግም ሰነድ ቀረበ


የድርጅቶቹ ስምና አርማና
የድርጅቶቹ ስምና አርማና

በየአራት ዓመቱ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት የአገራት የሰብዓዊ መብት መገማገሚያ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ለመገምገም የሚያስችል ሰነድ ቀረበ። ሰነዱን ካቀረቡት የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውስጥ፤ ሲቪከስ፣ሲፒጄ፣ዲፌንድ ዲፌንደርስ፣አርቲክል 19፣አክሰስናው፣ ፔን ኢንተርናሽናልና ኢመድህ ይገኙበታል።

በየአራት ዓመቱ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ ተሳታፊ ኾና ትቀርባለች፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ውይይት የሚደረገው ከ197 በላይ የዓለም አገሮች መካከል ሲኾን አገራቱ የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን በሚመለከት ሪፖርት የሚያቀርቡበት እንዲኹም የሚቀርብባቸውን ወቀሳና ትችት አዳምጠው የሚያሳሽሉትን ‹‹አሻሽላለሁ›› የሚሉበት ያልተስማሙበትን ደግሞ ያልተስማሙበትን ምክንያት የሚያስረዱበት ስብሰባ ነው፡፡

አገራቱ እንዲያሻሽሉ የሚነገራቸውና ምክረ ሐሳብ የሚቀርበው በሰብዓዊ መብት ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች አጠናቅረው በሚያቀርቡት ሪፖርት መሰረት ነው። ከዚያም ከአራት ዓመት በኋላ ሲመለሱ አሻሽለው እንደሆነ ወይም ደግሞ የባሰ ሁኔታ ተፈጥሮ እንደሆነ ይጠየቃሉ።

ከአራት ዓመት በኋላ ዘንድሮ ለሚደረገው ሪፖርትም ዘጠኝ የሚሆኑ ድርጅቶች ኢትዮጵያን የተመለከተ ሰነድ አደራጅተው አቅርበዋል። በዚህ ሰነድ ውስጥ ኢትዮጵያ መሻሻል አሳይታበታለች የተባለው ተጠቅሷል። በቀጣይ ልያሻሽል ይገባታል የተባለውም በምክረ ሐሳብ ሰፍሯል።

ከእነዚህ ድርጅቶች ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያን የሚመሩት አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ስለሰነዱ ተጠይቀዋል።

(ቃለምልልሱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ የሚገመግም ሰነድ ቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:29 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG