ባለፈዉ ዓርብ በኬንያዉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በፖለቲካ ተቃዋሚያቸው ራይላ ኦዲንጋ መካከል የተደረገው ሥምምነት ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ ጥምር አባላት አላካተተም ሲሉ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ ጥምር ናሽናል ሱፐር አሊያንስ አባላት ተናገሩ።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከተቃዋሚዉ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጋር ዛሬ በኬንያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ተወያዩ። ከውይይታቸዉ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኬንያታ የአገራቸዉን የወደፊት ዕጣ ፈንታን የተሳካ ለማድረግ መሪዎች መነጋገርና መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
የታንዛኒያ ፍርድ ቤት በ84 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ የ3 ዓመት እሥራት አስተላለፈ። ኢትዮጵያዊያኑ የተያዙት በታንዝኒያ ማዕከላዊ ክፍል “ኢሪንጋ” በሚባል ቦታ ሲሆን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ሊያልፉ ሲሉ ነው - በታንዛኒያ ፖሊስና በሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ኃላፊዎች የተያዙት።
በኬንያ ባሉ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ዕርዳታ በመቅነሱ ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናገሩ።
ባለፈው ሳምንት መጀመርያ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባር ድርድር ሁለቱ ተደራዳሪዎች ከስምምነት ሳይደርሱ ተጠናቋል።
ጥቅምት 16 2010 ዓ/ም ድጋሚ የተደረገውን የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ኡሁሩ ኬንያታ ኬንያን ለሁለተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሓላ ፈጸሙ።
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 16 በድጋሚ የተደረገውን የኬንያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት አፀና። በዚህም ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ያሸነፉትን ምርጫ አፅድቋል።
ኬንያ፣ የሶማሊያ ስደተኞች ይኖሩበት የነበረውን የደዳብ ካምፕ ሠፈሮች እየዘጋች መሆኗን ስደተኞች ተናገሩ። ባለፈው ዓመት "ካምብዮስ" የተባለ የደዳብ ሰፈር የተዘጋ ሲሆን፥ በሚቀጥለው ዓመትም “F2” የተባለው ሰፈር ሊዘጋ እንደሆነ ስደተኞቹ ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።
137 ኢትዮጵያዊያንን በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ እንዲገቡ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ዛሬ ኬንያ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የኬንያ ፖሊስ ባለፈዉ አርብ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸዉ 137 ህገ ወጥ የኢትዮጵያዉያ ፍልሰተኞች ላይ ትላንት ከሰዓት ብይን ሰጠ። በፍርዱም እያንዳንዳቸዉ 300 የአሜርካን ዶላር ወይም የ 6ወር እሥራት ተላልፎባቸዋል።
የኬንያ ምርጫ ቦርድ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ያጣጣሉትን ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ። በምርጫው ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ ደምፅ አግኝተው ማሸነፋቸውን የኬንያ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽነር ዋፉላ ቸቡካቲ ገልፀዋል።
በናይሮቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሠብ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግሥት የኬንያ ፖሊስን ተጠቅሞ በስደተኛው ላይ ጫና ማድረጉን አላቆመም በማለት ተናገሩ።
ካሎበዬይ በሰሜን ምዕራብ ኬንያ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ አዲስ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ነዉ።
የኬንያ ሲቪል ማኅበረሰብ ጥምረት የኬንያ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ላይ ምርመራ እንዲካሄድ በመጠየቅ ትላንት ማምሻዉ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን የፊታችን ጥቅምት 7 አዲስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚያካሄድ ገልጿል፡፡
የአለፈዉ ዓርብ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት ውሳኔ በኬንያታ ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታ ሲያሳድር በተቀናቃኛቸዉ በራይላ ደጋፊዎች ዘንድ ግን ልዩ ደስታን ፈጥሯል።
ኬንያ በቅርቡ ያካሄደችው ፕሬዘደንታዊ የምርጫ ሂደት ፍትሃዊ አልነበረም ሲል የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውጤቱን ውድቅ አድርጓል፤ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ወስኗል።
ኬንያ ፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም የሚከለክለዉን ህግ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች
14ኛዉ የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ዕድገት ጉባኤ በናይሮቢ በመካሄድ ላይ ነዉ።ትላንት በተጀመረው ጉባኤ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙንን ጨምሮ የበርካታ አገሮች መሪዎች ተገኝተዋል።
ናዝራዊ ኢያሱ አባቱ ኢትዮጵያዊ እናቱ ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው። ወላጆቹ እኤአ ከ2001 ዓ. ም. ጀመሮ በኬንያ በስደት ነው የኖሩት። ኬንያ እንደመጡ ከናይሮቢ 180 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘዉ ናሮክ ከተማ ኑሯቸውን መሰረቱ።
ተጨማሪ ይጫኑ