በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች በታንዛኒያ የ3ዓመት እሥር ተፈረደባቸው


የታንዛኒያ ፍርድ ቤት በ84 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ የ3 ዓመት እሥራት አስተላለፈ። ኢትዮጵያዊያኑ የተያዙት በታንዝኒያ ማዕከላዊ ክፍል “ኢሪንጋ” በሚባል ቦታ ሲሆን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ሊያልፉ ሲሉ ነው - በታንዛኒያ ፖሊስና በሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ኃላፊዎች የተያዙት።

የታንዛኒያ ፍርድ ቤት በ84 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ የ3 ዓመት እሥራት አስተላለፈ። ኢትዮጵያዊያኑ የተያዙት በታንዝኒያ ማዕከላዊ ክፍል “ኢሪንጋ” በሚባል ቦታ ሲሆን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ሊያልፉ ሲሉ ነው -በታንዛኒያ ፖሊስና በሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ኃላፊዎች የተያዙት።

ኢትዮጵያዊያኑን በታፈነ መኪና አጉሮ ሲያጓጉዟቸዉ የነበረ ሾፌር ሲያመልጥ ፖሊስ ከፍልሰተኞቹ ጋር የነበረ ሐሰን ፌሩዝ የሚባል ታንዛኒያዊን በቁጥጥር አውሎታል።

ሆፕ ካዋዋ በታንዛኒያ የኢሪንጋ ግዛት ኢሚግሬሽን ኃላፊ

“ኢትዮጵያዊያኑን በቁጥጥር ሥር ስናውላቸዉ ከ84ቱ ውስጥ 12ቱ ራሳቸውን ስተዉ ስለ ነበር፤ ወደ ኢሪንጋ ሆስፒታል ተወስዶ ህክምና እንዲደረግላቸው ተደርጓል” ሲሉ ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በታንዛኒያ ኢምባሲ የሌላት ሲሆን የአሜርካ ድምፁ ጉዳዩ የሚመለከተውን ኬንያ ያለውን የኢትዮጵያን ኢምባሲ ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

ሙሉውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች በታንዛኒያ የ3ዓመት እሥር ተፈረደባቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG