ዋሺንግተን ዲሲ —
የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከተቃዋሚዉ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጋር ዛሬ በኬንያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ተወያዩ። ከውይይታቸዉ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኬንያታ የአገራቸዉን የወደፊት ዕጣ ፈንታን የተሳካ ለማድረግ መሪዎች መነጋገርና መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
ተቀናቃኛቸው ራይላም ኬንያ በጎሳ ክፍፍል በመጎዳቷ ለዚህ መፍትሄ ለመፈለግ አብሮ ለመሥራት መስማማታቸውን ነው የተናገሩት።
ኬንያታና ራይላ ኬንያን እየጎዳ ስላለው ስለ ሙና፥ የፀጥታ ችግር፣ የጎሳ ግጭት፣ ፍትሃዊ ሀብት ክፍፍል አለመኖርና የመንግሥት መዋቅሮች ከህዝብ ፍላጎት ጋር አለመጣጣም ዙርያ ተወያይተው ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ይህን ስምምነታቸዉን የሚያስፈፅም አዲስ ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል።
ሙሉውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ