በኢተርኔት አማካኝነት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር የወጣውን የሳይበር ደህንነት ዐዋጅ ሕጋዊ እንዲሆን የኬንያው ፕሬዝዳንት ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በፊርማቸው ያፀደቁት ሲሆን ዐዋጁ ተላልፈው ወንጀል በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ እስከ 25 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ የሚያስቀጣ ቅጣት ደንግጓል።
ዐዋጁ በመረጃ ነፃነት ላይ ጫና ሊያሳርፍ እንደሚችል በመግለፅ በኬንያ ያሉ ጦማሪዎች፣ ለሚዲያ ነጻነት የሚሟገቱ ግለሰቦችና ድርጅቶች እየተቹት ይገኛሉ። ይህ ትላንት በኡሁሩ ኬንያታ የጸደቀዉ ዐዋጅ ተጨባጭ ያልሆነ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይም የ2 ዓመት እሥራት ወይም የ5ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ ቅጣት እንደሚቀጡም ደንግጓዋል።
ሮበርት አላይ ጦማሪ ነዉ፥ ሲጀምር ኬንያ ስለ ነጻ ፕሬስ በግልፅ የሚያስቀምጥ ህገመንግስት እያላት ለምን ይህ አዋጅ እንደተፈለገ ግልፅ አይደለም ይላል። አክሎም በተለይ በመረጃ ነጻነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ያለዉን ስጋት ገልጿል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ