በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ የስደተኞች ካምፕ የሚኖሩ ዕርዳታ በመቅነሱ ለረሃብ ተጋለጡ


የካኩማ ስደተኞች ካምፕ
የካኩማ ስደተኞች ካምፕ

በኬንያ ባሉ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ዕርዳታ በመቅነሱ ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናገሩ።

በኬንያ ባሉ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ዕርዳታ በመቅነሱ ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናገሩ። በስሜን ምዕራብ ኬንያ በሚገኘዉ የካኩማ ስደተኞች ካምፕ ለ12 ዓመት የኖሩ የ5 ልጆች አባት ዕርዳታው በመቀነሱ ቤተሰባቸውን መደጎም እንዳልቻሉ ተናግረው፣ በካምፑ ያሉ ስደተኞች በችግር ላይ መሆናቸውን ያስረዳሉ።

በቅርቡ በኬንያ ያሉ ስደተኛ ካምፖችን የጎበኙት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ለስደተኞች የሚደረገው የምግብ ዕርዳታ መቀነሱ እንዳሳሰባቸዉ ገልፀው፣ ጉዳዩን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመወያየት እንደሚፈቱ ቃል ቢገቡም፥ ስደተኞች ግን እስካሁን ምንም የተሰተካከለ ነገር አለመኖሩን ይገልፃሉ።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በበኩሉ ችግሩ የዕርዳታ ገንዘብ በመቀነሱ የተከሰተ መሆኑን ገልጿል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኬንያ ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ማርቲን ካሪሚ የምግብ እጥረቱ የተከሰተዉ ድርጅታቸው በቂ ፈንድ ባለማግኘቱ እንደሆነ ገልፀው፣ በኬንያ ያሉ ስደተኞችን ለመደጎም የዓለም ምግብ ፕሮግራም የጠየቀዉ 28 ሚሊዮን ዶላር ካልተገኘ ችግሩ ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኬንያ የስደተኞች ካምፕ የሚኖሩ ዕርዳታ በመቅነሱ ለረሃብ ተጋለጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG