በጉጂና ጌዴዖ ዞኖች ዜጎችን በማፈናቀል፣ ንብረት በማውደምና በመግደል የተጠረጠሩ ከ270 በላይ ተጠሪጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢፌዲሪ ሠላም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
"ከአሁን በኋላ ከእናንተ የሚጠብቀው ጥያቄ ተፈናቅልናል ዕርዳታ አቅረቡልን ሳይሆን ባለንበት አካባቢ ውሃ አስገቡልን፣ ትምህርት ቤት አስገንቡልን የሚል መሆን አለበት" ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ዳይሬክተርና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፡፡
በክልል የመደራጀት መብትና በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በብሄሩ ተወላጆች ላይ በማንነታቸው የሚፈፀም ጥቃት የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አርብ ዕለት በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡
ከምግብ እጥረትና ከተጓዳኝ እክሎች የተነሳ ባለፉት ሰባት ሳምንታት ብቻ 18 ህፃናትና 4 አዋቂዎች መሞታቸውን የጌዲዖ ዞን ጤና መምሪያ ይፋ አደረገ፡፡ 2 ሺህ 239 ህፃናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸው የታወቀ ሲሆን 374 ህፃናት በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ስለሚገኙ ማገገሚያ ማዕከል ገብተዋል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ የተፈናቀሉ የጌዴኦ ተወላጆች አሁንም ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡
ነገ በዲላ ከተማ ሊካሄድ የነበረ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ምሽት ተከለከለ፡፡
ከምስራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ከተፈናቀሉ የጌዴዖ ብሄር ተወላጆች ውስጥ በመጀመሪያው ዙር 15 ሺህ ዜጎችን ወደቀያቸው ለመመለስ ከትናንት አንስቶ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
በደቡብ ክልል በሃዲያና ጉራጌ ዞኖች መካከል የሚገኘው ጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ያሉ ጉማሬዎች እየሞቱ መሆኑ ታውቋል፡፡
በሃዋሳ ከተማ ከእግር ኳስ ጨዋታ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ግጭት እጃቸው አለ ያላቸውን 37 ሰዎችን ማሰሩን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ከምሥራቅና ከምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተፈናቀሉ የጌዴኦ ብሄረሰብ ተወላጆች ለተለያዩ በሽታዎችና ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን እየተናገሩ ናቸው።
የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ ከአምስት ሺህ በላይ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ ከመቱ ሁለተኛ ሳምንት መያዙን ተናገሩ፡፡
የሃዋሳ ከተማ ዕጣ ፈንታ በአብሮነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በወቅታዊ ፖሊቲካ ጉዳዮች ለነዋሪዎች ሥጋት ሊሆን እንደማይገባ የደቡብ ክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ተናገሩ፡፡
ፌደራል መንግሥቱ ለጌዴኦ ቀውስ ግልፅና ዘላቂ መፍትኄ እንዲሰጥ የጌዴዖ ምሁራን ማኅበር ጠይቋል። በሕዝቡ ላይ ለደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ተመጣጣኝ ትኩረት በክልልና በፌደራል መንግሥት ባለመሰጠቱ ችግሩ የከፋ መሆኑን በመግለፅ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩት ምሁራን መንግሥትን በምክንያትነት ከስሰዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ብቻ በተሳተፉበት ትዕይንተ ሕዝብ ላይ፣ ብሄረሰቡ ከነበረበት የደቡብ ህዝቦች እና ብሄረሰቦች ክልል ተነጥሎ በአፋጣኝ ክልልነት ዕወቅና እንዲሰጠው የሚጠይቁ መፈክሮች እና መልዕክቶች ተሰምተውበታል፡፡
በመስቃንና በማረቆ ብሄረሰቦች መካከል ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ግጭት ቀስቃሽ ተግባር እየፈፀመ ነው ሲሉ የማረቆ ብሄሰብ ተወካይ ነን የሚሉ ሰዎች መንግሥትን ከሰሱ፡፡
በጋሞ ዞን ሜሎ ወረዳና ባስኬቶ ልዩ ወረዳ የማንነት ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ከ37 ሺህ በላይ የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ተፈናቃዮች በረሃብ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገለፁ።
በማኅበራዊ መገናኛዎች ፎቶዋቸው እየተዘዋወረ ነው፡፡ ወ/ሮ ሙሉነሽ ለጌዴኦ ተፈናቅዮችና በረሃብ ለተጎሳቆሉት ትኩረት እንዲሰጥ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ወ/ሮ ሙሉነሽ አሁን ዲላ ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ ሆስፒታል ከመግባታቸው በፊት በተጠለሉበት፣ እንደነገሩ በተጣለ ታዛ ሥር፣ ኩርምት ብለው ያሉበትን ሁኔታና የገጠማቸውን ፈተና ለሪፖርተራችን ዮናታን ዘብዲዮስ አጋርተውታል፡፡
ከምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ ዞኖች ተፈናቅለው እየተንገላቱ ላሉ ሰዎች ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ የጌዴኦ አባገዳ ጠየቁ፡፡ አባገዳ ደንቦቢ ማሮ ጥያቄውን ያቀረቡት "ዳራሮ" በሚባለው የጌዴኦ ብሄር ዓመታዊ የምሥጋናና የፀሎት ክብረ በዓል ላይ ነው፡፡ ለተፈናቀሉት ወገኖቻቸው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡
ካለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ጀምሮ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው በጊዲዖ ዞን በገደብ ወረዳ፣ በጎቲቲ ቀበሌ፣ ባንቆራ፣ ጮርሶ፣ ቀርጫ፣ ይርጋጨፌና ዲላ ውስጥ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች፤ ለስምንት ወራት ያህል የምግብ ርዳታን ባለማግኘታቸው ለረሃብና ለተላላፊ በሽታ መጋለጣቸውን ገለፁ። በረሃቡ የሞቱ ሕፃናት አሉ ብለዋል።
በሀዋሳ ከተማና ሲዳማ ዞን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅት ተዘግተው ዋሉ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ