በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ጉባዔ ዛሬ በገጠመው ተቃውሞ ተቋረጠ፡፡
የገዳ ስርዓት አንዱ አካል የሆነው የኦሮሞ ሴቶች "ስንቄ" ባህል የእርቅና የሰላም ተምሳሌት ነው፡፡
ሥርዓቱ በህገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ጣልቃ መግባቱ የለውጡን አካሄድ ጥያቄ ውስጥ እያስገባ ስለመሆኑ ማሳያ ነው አለ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸው ወቅት አጠቃላይ የፓርኩ እንቅስቃሴ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ሁለት ኩባኒያዎችን የምርት ሂደት ተዘዋውረው ቃኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ባለፈው ዓመት በኬንያ ባደረጉት ጉብኝት በሀገሮቹ መካከል ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መስማማታቸው ይታወሳል።
በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክና በከተማው ነጋዴ ማኅበረሰብ መካከል የንግድ ግንኙነትና ትስስር እንዳልተፈጠረ የሃዋሳ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማኅበር ምክር ቤት ‘አድርጌዋለሁ’ ባለው ጥናት አስታውቋል፡፡
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱንና የህዝበ ወሳኔ ቀን አለመገለፁን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡ ሰልፉ በሲዳማ "ቀጣላ" ባህላዊ ስርዓት የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ መንገድ ተጠናቅቋል፡
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱንና የህዝበ ወሳኔ ቀን አለመገለፁን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡ ሰልፉ በሲዳማ "ቀጣላ" ባህላዊ ስርዓት የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ መንገድ ተጠናቅቋል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራን በተመለከተ "ዜማችን ፣ ቅዳሴያችንና መዝሙራችን ሰላም ነው" አሉ በሀዋሳ ከተማ ጉብኝት ያደረጉት የኤርትራ ባህል ቡድን አባላት።
ከአሁን ወዲያ ኢትዮጵያና ኤርትራ በተመለከተ ዜማችን ፣ ቅዳሴያችንና መዝሙራችን ሰላም ነው አሉ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የኤርትራ ባህል ቡድን፡፡
በኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛት የሴቶች ሰብዓዊ መብትና ሥነ ልቦና ፈተና እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/ ሊቀ መንበር ሌንጮ ለታና ምክትል ሊቀ መንበር ዶ/ር ዲማ ነጎ ከ40 ዓመታት በፊት አብረው ትግል ለጀመሩት ለሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ መስራችና ታጋይ ለአቶ ወልደአማኑኤል ዱባለ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ ይርጋለም ከተማ ድረስ በመሄድ መካነ መቃብራቸው ላይ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡ "ወልደአማኑኤል ለሲዳማ ህዝብ ነፃነት የሞተ፤ ለአሮሞና ሲዳማ ህዝቦች አንድነት ዋጋ የከፈለ ታጋይ ነው" ዶ/ር ዲማ ነጎ
"የሁሉም ኢትዮጵያውያን ማንነት የሚታስተናግድ ኢትዮጵያ መገንባት ያስፈልጋል" የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኦዴግ ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታ፡፡
የቡርጂ ወረዳ መንግሥት ሰራተኞች ሥራ የማቆም አዱማ ከመቱ ሁለተኛ ሳምንት ይዟል፡፡
"ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ያላትን የተፈጥሮ ሃብት አስተባብሮ መምራት የሚችል መንግሥት ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
በቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሲቪሎች መቁሰላቸውን የከተማው ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር አመልክቷል፡፡
የአገር ሸማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶችና ወጣቶች የተገኙበት የሰላም ኮንፈረንስ በይርጋለም ከተማ ተካሂዷል፡፡
የኦነግ ታጣቂዎች ዛሬ አራት ሰዎችን አንደገደሉ የአማሮ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የተገደሉት ሰዎች ከአርባ ምንጭ በኮንሶ ዞን አድረገው ቡርጂ ወረዳ አቋርጠው ወደ አማሮ ኬሌ ይጉዋዙ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ በካምባታ ጣምባሮ አርሶአደሮች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት ያሳየውን ቸልተኝነት በመቃወምና ሀዘናቸውን በመግለፅ የዞኑ ህዝብ አደበባባይ ወጣ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ