በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደቀያቸው የተመለሱ የጌዴዖ ተፈናቃዮች


ወደቀያቸው የተመለሱ የጌዴዖ ተፈናቃዮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:29 0:00

ወደቀያቸው የተመለሱ ዜጎች ገበያ በመገበያየት የቀድሞ የህዝብ ለህዝብና ማህበራዊ ግንኙነት መጀመራቸውን በጌዴዖ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የጭርቁ ቀበሌ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በቀበሌው ቤቶቻቸው ከተቃጠለባቸው ዘጠኝ መቶ አባወራዎች ውስጥ የአምስት መቶ አባወራዎችን ቤት ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እንደሰራላቸው የሚገልፁ ዜጎች ወንጀለኞች ባለመያዛቸው ኑሯቸውን በሥጋት እንደሚመሩ አስረድተዋል፡፡

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ከጉጂና ከጌዴዖ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ሁለት ቢሊዮን የሚደርስ ብር ወጪ ማድረጉን ገልፆ አሁንም ድጋፉ ይቀጥላል ይላል፡፡

ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑን የሚገልፀው የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስቴር ዜጎችን አፈናቅለዋል ፤ ሰው ገድለዋል በማለት የሚጠረጥራቸውን ከ270 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ከ280 ሺህ በላይ ዜጎችም ወደቀያቸው መመለሳቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG