በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ


የሲዳማን ክልል እንሁን ጥያቄ ተከትሎ በዞኑ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሁከት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡

በሁከቱ እስከ አሁን የዘጠኝ ሰው ህይወት አልፋል፤ በርካቶች ቆስለዋል፤ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል፡፡ የሁከቱ ሰለባ የሆኑ እንደሚናገሩት በአንዳንድ በሲዳማ ዞን ከተሞተሞች ተቃውሞው ዛሬ መልኩን ቀይሮ ማንነትን በመለየት፣ የመኖሪያ ቤትና ንብረትላይ ጥቃት ደርሷል፡፡ መንግሥት ተጨማሪ ኃይል በማስገባት ሰላማችንና ደኅንነታችንን ያረጋግጥ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ትናንት በሀዋሳ ከተማ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፣ ዛሬ ሀዋሳ የተረጋጋች መሆኑ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የሲ አን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከአስር በላይ ሰዎች በመልጋ ወረዳና አካቢው ሞተዋል ብለዋል፡፡ በግጭቱ ማዘናቸውን የገለፁት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ህዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ችግሩን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የፀጥታ ኃይል እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG