በምዕራብ ኦሮምያ ማዘዣ ማዕከል ታስረው የነበሩ የነቀምቴ ወንጀል መከላከል ኃላፊና የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሃኪም ተለቀቁ፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ማንዱራ ወረዳ ሰባት ሰዎችን በመግደል የተጠረጠሩ 14 ግለሰቦችን መያዙን የክልሉ ፀጥታና ሰላም ግንባታ ቢሮ አስታወቀ፡፡
በደምቢዶሎ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ጫካ ያለው ታጣቂ ቡድን ከመንግሥት ጋር ተደራድሮ ሰላም እንዲወርድ ተጠየቀ፡፡
ቴርኪዲ የስደተኞች መጠለያ መንደር ከጋምቤላ 45 ኪሜ ርቀት ላይ ይገኛል። በካምፑ ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች ይገኛሉ።
ዛሬ ታስቦ የዋለውን የዓለም ስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ናኮር መልካ በጋምቤላ ተገኝቶ ከአንድ ወጣት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡
ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ትናንት ምሽት በአንድ ሆቴል ላይ በተጣለ የእጅ ቦምብ አደጋ አንድ ሰው ተገድሏል፤ ዘጠኝ ሰው መቁሰሉ ተነግሯል።
በነቀምቴ ትናንት ማታ አንድ ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦምብ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።
በድርቅ ምክንያት ከሀረርጌ ተፈናቅለው ሆሮ ጉዱሩ ዞን ሀሙሩ ወረዳ የሰፈሩ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች ድጋፍ ቢደረግልንም ችግራችንን በዘላቂነት የሚፈታ ምቹ የግብርና መሬት እንዲሰጠን እንፈልጋለን አሉ::
ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ነፃነት ሸማቂዎች ባለፈው ሰኞ ሙጊ ውስጥ የእጅ ቦንብ ወርውረው ሥድስት ሰዎች ገደሉ ሲሉ የቄለም ወለጋ ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ተናገሩ፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን ፀጥታና ደኅንነት ፅህፈት ቤት ከሁለት ወራት በፊት በነጆ ወረዳ በማዕድን ጥናት ላይ የሚሰሩ አምስት ሰዎችን በመግደል የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦችን ቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡
የኦሮምያ እና ጋምቤላ ክልሎች የጋራ የህዝብ ለህዝብ መድረክ በጋምቤላ ትናንት መካሄዱ ታወቀ::
ምዕራብ ወለጋ ላሎ አሳቢ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ “አሥር ሰዎች የጭነት መኪና ላይ አሸዋ ሲጭኑ ተገደሉ ሲል አንድ ከቅርብ ርቀት አየሁ” ያለ ግለሰብ ለቪኦኤ ቃሉን ሰጥቷል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዳንጉር ወረዳና አማራ ክልል ጃዊ ወረዳ የተፈጸሙ ግድያዎችን የሚያጣራ አጣሪ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን የክልሎቹ ባለሥልጣኖች አስታወቁ።
የኦሮሚያና አማራ ክልሎች ህዝብ ለህዝብ የውይይት መድረክ በአምቦ ተካሄደ። ኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት መጠናከር ኢትዮጵያን ከፍ ያደርጋታል ብለዋል:: የአማራ ክልል ርእሰ መስትዳድር ዶክትር አምባቸው መኮንን ኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ላይ ያለው ጥቅም ተግባራዊ እንዲሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል::
የኦሮሚያና አማራ ክልሎች ህዝብ ለህዝብ የውይይት መድረክ በአምቦ ተካሄደ።
አዲሱ የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ ከደምቢ ዶሎና ቄለም ወለጋ ዞን የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል። ቪኦኤ ያነጋገራቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች በዞኑ ሰላም እንደሚያሰፍኑ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ የወለጋ ስታድዮም የመጀመሪያ ምዕራፍ መረቁ። ከነቀምቴና ምስራቅ ወለጋ ዞን ከተወከሉ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ከዓመታት በፊት ከተለያዩ የአምቦ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሎጆች የተመረቁ ተማሪዎች ሥራ ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን እየገለፁ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ አንደኛ ዓመታቸውን በማሰመልከት ቪኦኤ የነቀምቴ ነዋሪዎች የሰጡት አስተያየት።
በምዕራብ ወለጋ፤ ነጆ ወረዳ ከትናንት በስቲያ አምስት ሰዎች የተገደሉት የአባ ገዳዎችንና የሃገር ሽማግሌዎችን ጥሪ ባልተቀበሉ የሸኔ ኦነግ ታጣቂዎች ነው ሲል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ