የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን በቄለም ወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚለው ወሬ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገለፁ በማለት ያስተላለፈው ዜና ከእውነት የራቀ ነው ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለቪኦኤ አስታወቀ፡፡
አፋን ኦሮሞ የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ቢሆን ያለው እድሎች ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱ ታወቀ፡፡
ሁለት የአምቦ ከተማ እማወራዎች “ኡቡንቱ” .. (የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪቃው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም “ለመኖሬ ምክኒያቱ አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ” የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው።
ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ የቀድሞ ታጣቂዎች አቀባበል ለማድረግ የተቋቋመው ኮሚቴ በምዕራብ ወለጋ ዞን መነ ሲቡ ወረዳ እየተቀበለ ማስተናገድ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ጋር ከምዕራብ ወለጋ ቤጊ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
በምዕራብ ወለጋ ውስጥ "የቤተሰቦቻችን አባላት ታስረዋል፤ ፍርድ ቤትም አልቀረቡም" የሚሉ ሰዎች አቤቱታ እያሰሙ ነው።
የቤኒሻንጉል ክልል ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ 203 ፀረ ሰላም ኃይሎች ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ፡፡
ከቤኒሻንጉል ጉምዝ በሎ ጃገንፎይና ሶጌ ወረዳዎች ተፈናቅለው በነቀምቴ ከተማ ሠፍረው የሚገኙ ቪኦኤ ያነጋገራቸው አንዳንድ ተፈናቃዮች - መንግሥት ዘላቂ መፍትሄ ይስጠን እያሉ ነው።
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮና በምሥራቅ ወለጋ ሊሙ ገሊላ ወረዳዎች ቁጥራቸው ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ፡፡
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ መሪዎችና አባሎቼ እየታሠሩ ናቸው ሲል አቤቱታ አሰማ።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ካማሺ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች የትራንስፖርት እጥረትና የኑሮ ውድነት እንደገጣማቸው ተናገሩ፡፡
የአምቦ መሰአናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ባካሄዱት ሰልፍ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎቸ አርቅ እንዲያካሂዱ ጥሪ አቀረቡ፡፡
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሻምቡ ከተማ በማዘዣ ማዕከል ተይዛ ለሥድስት ቀናት እስር ላይ የቆየችው ጫልቱ ታከለ መፈታቷ ታወቀ።
ምዕራብ ኦሮምያ ውስጥ ለአሥራ ሁለት ዓመት ገደማ ታሥራ ቆይታ ከአንድ ዓመት በፊት የተፈታችውን ጫልቱ አቤቱ ጨምሮ ብዙ ሰው መታሠሩ ተገልጿል።