በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ ወለጋ በማዕድን ጥናት ላይ የሚሰሩ ሰዎችን በመግደል የተጠረጠሩ ተያዙ


የምዕራብ ወለጋ ዞን ፀጥታና ደኅንነት ፅህፈት ቤት ከሁለት ወራት በፊት በነጆ ወረዳ በማዕድን ጥናት ላይ የሚሰሩ አምስት ሰዎችን በመግደል የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦችን ቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” የሚላቸው ታጣቂ ቡድን አባላት እንደሆኑ የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡

የቄለም ወለጋ ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዲፒ የሕዝብ ግንኙንት ኃላፊ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሽኔ የታጠቁ ኃይሎች የመንግሥት ሰዎችን ይገድላሉ፣ ያሰቃያሉ ሲሉ ከሷል፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ተዋጊዎች የምዕራብ ዞን ጦር መሪ “መሮ” በሚባል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ኩምሳ ድሪማ ግድያውን አልፈፀምንም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

በምዕራብ ወለጋ በማዕድን ጥናት ላይ የሚሰሩ ሰዎችን በመግደል የተጠረጠሩ ተያዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG