በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ነቀምቴ አንድ ሆቴል ላይ በተጣለ የእጅ ቦምብ የሰው ሕይወት አለፈ


ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ትናንት ምሽት በአንድ ሆቴል ላይ በተጣለ የእጅ ቦምብ አደጋ አንድ ሰው ተገድሏል፤ ዘጠኝ ሰው መቁሰሉ ተነግሯል።

ባለፈው ሣምንትም የዚሁ ትናንት ጥቃቱ የተፈፀመበት “ሶከር” የሚባል ሆቴል ባለቤት አቶ ፈለቀ ዓለሙ ንብረት በሆነ ሌላ ሆቴል ላይ ተመሣሣይ አደጋ ተጥሎ ሰባት ሰው መቁሰሉ ተዘግቧል።

ቦምቡ ትናንት ሆቴሉ ላይ መወርወሩን ለቪኦኤ ያረጋገጥት የነቀምቴ ምክትል ከንቲባ አቶ ጫላ ገመዳ የቆሰለው ሰው ሰባት መሆኑን ተናግረዋል።

እስከአሁን የተያዘ ተጠርጣሪ ወይም ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ የለም።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ነቀምቴ አንድ ሆቴል ላይ በተጣለ የእጅ ቦምብ የሰው ሕይወት አለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG