በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በነቀምቴ አንድ ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦምብ ሰባት ሰዎች ቆሰሉ


በነቀምቴ ትናንት ማታ አንድ ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦምብ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

ጥቃቱን ተከትሎ በፍተሻ ላይ የነበረ የመንግሥት ታጣቂ እራት በልቶ ከጓደኞቹ ጋር ወደ ማደሪያው ሲመለስ የነበረ አንድ የከተማው እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች ላይ ተኩሶ ገድሎታል ሲሉ የቡድኑ አሠልጣኝ ከስሰዋል።

የሆቴሉ ሥራ አስኪያጅ በፍንዳታው ሰዎች መቁሰላቸውን ገልፀው ብዙ ንብረትም መውደሙን ተናግረዋል::

የከተማው ኮምዩኒኬሽንስ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ በቦምቡ ፍንዳታ ሰዎች መቁሰላቸውን አምነው የአድራጊው ማንነት እንዳልታወቀ ገልፀዋል::

በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሦስት ሰዎች መያዛቸውንም ተወካይዋ ጨምረው ተናግረዋል::

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በነቀምቴ አንድ ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦምብ ሰባት ሰዎች ቆሰሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:40 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG