በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምዕራብ ወለጋ ላሎ አሳቢ ወረዳ በደረሰው አደጋ የተጠረጠሩ ታሰሩ


ምዕራብ ወለጋ ላሎ አሳቢ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ “አሥር ሰዎች የጭነት መኪና ላይ አሸዋ ሲጭኑ ተገደሉ ሲል አንድ ከቅርብ ርቀት አየሁ” ያለ ግለሰብ ለቪኦኤ ቃሉን ሰጥቷል።

የዞኑ የፀጥታ ፅህፈት ቤት ስለጉዳዩ እያጣራ መሆኑን ጠቅሶ “በሥፍራው ሲታኮሱ የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” በማለት ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል::

ትጥቅ አልፈታም፤ እስከመጨረሻው እዋጋለሁ ያለ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂ አንጃ በአካባቢው የሚንቀሳቀስ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን “ደበሌ የሚባል የዚሁ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አፈንጋጭ ታጣቂዎች የምዕራብ ኦሮምያ ዞን መሪ ነው” የተባለ ግለሰብ በበኩሉ “ሰዎቹን የገደሉት የመከላከያ አባላት ናቸው፤ የተያዘ የኦነግ ታጣቂ የለም” ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ምዕራብ ወለጋ ላሎ አሳቢ ወረዳ በደረሰው አደጋ የተጠረጠሩ ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:50 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG