በነቀምቴ ከተማ ባለፈው ቅዳሜ አንድ ወጣት በመንግሥት ታጣቂ ተገደለ ሲሉ አባቱ ገልፀዋል።
ክብረ በዓሉን በማስቀደም በዓሉ የሚከበርበትን ቦታ ለአፀዱ የአምቦ እስልምና ሃይማኖት ተከታዮችም ምስጋና ቀርቧል።
በአምቦ ከተማ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለው ተቃውሞ ሰልፍ የሰዎችን ህይወት ቀጠፈ ሲሉ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ከተሳተፉ መካከል ተናገሩ፡፡
"የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ጃዋር መሐመድ ጠባቂዎችን ትናንት ሌሊት ከሥራቸው በኃይል ለማንሳት የተደረገውን ሙከራ" እንቃወማለን የሚሉ ወጣቶች ዛሬ በአምቦ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ታወቀ፡፡
የቡና ጥራትን በማስጠበቅ የቡና አምራች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግና የተሻለ የውጭ ምንዛሪን ለማግኘት ያለመ የውይይት መድረክ በነቀምቴ ተካሄደ::
"በመንገድ ግንባታ ምክንያት የምንኖርበትን የመንግስት ቤት ቶሎ እንድናፈርስ መወሰኑ ቅሬታ አሳድሮብናል" ሲሉ አንዳንድ የአምቦ ከተማ 03 ቀበሌ ነዋሪዎች ተናገሩ:: "ግንባታው ከ100 በላይ አባ ወራዎችን ስለሚያስነሳ ቤት አልባ ያደርገናል" ብለዋል::
ላለፉት ሦስት ወራት በነቀምቴ ኩምሳ ሞረዳ ቤተ መንግሥት ታስረው የሚገኙ ግለሰቦች እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው እንዳሳሰባቸው ከቤተሰቦቻቸው መካከል አንዳንዶቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል::
በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ “ማንነታቸው አልታወቀም” በተባሉ ታጣቂዎች ትናንት ማታ መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
በጅማ የተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ ሰሞኑን በተከሰተ በሽታ ሕይወት ማለፉን አንዳንድ የመጠለያው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የኦሮምያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጋራ የህዝብ ለህዝብ መድረክ በጊምቢ ከተማ ተካሂዷል።
በማህበራዊ መገናኛ ከ420 ሺ ብር በላይ በማሰባሰብ ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን በደብተርና እስክሪብቶ መደገፋቸውን "የነቀምቴ ልጆች" ፌስቡክ ገፅ አስተባባሪ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ወጣት ጂኔኑስ ፈቃዱ ፋርማሲስትና የወለጋ ዩኒቨርሲቲ መምሕር ነው:: ከሚያገኘው ደመወዝና ጓደኞቹን በማስተባበር ድጋፍ የሌላቸውን 20 የኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በገንዘብና የትምህርት ቁሳ ቁስ በማሟላት እንደሚያስተምር ይናገራል::
ዶክተር ኦሮሊያና ዳንኤል በግል ድርጅት የጥራት ተቆጣጣሪ ሆኖ ይሠራል። ከሶስት ወር በፊት "እህም" የተሰኘ የወግ መፅሐፍ ጽፎ ከ12 ሺ በላይ እትም ተሽጦለታል። ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ አገራትም መጽሐፉን ማዳረሱን ይናገራል:: የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መጽሐፉ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።
ከ8 ዓመት በፊት ከሐረርጌ ተፈናቅለው፣ በአሁኑ ጊዜ በሁሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ፣ ጎይቶ ቀበሌ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ ለአለፉት ሦስት ወራት የእህል ድጋፍ በመቋረጡ ከ10 በላይ ህፃናት በምግብ እጥረት ምክንያት መሞታቸውን ገለፁ፡፡
አራት የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በአሶሳ ስለ ሰላምና ልማት እየተወያዩ መሆኑ ተገለፀ።
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀሙሩ ጉዪ ቴቦ ቀበሌ የሰፈሩ ተፈናቃዮች "ላለፉት ሶስት ወራት የእህል ድጋፍ በመቋረጡ ከ10 በላይ ሕፃናት በምግብ እጥረት ሞቱ" ሲሉ ገለፁ፡፡
በቤኒሻንጉል ጉምዝ በሎ ጀጋንፎይ ወረዳ ውስጥ በግብርና ሥራ ላይ ነዋይ አፍሳሽ የሆኑ አንዳንድ ባለሃብቶች በፀጥታ ስጋት ምክንያት በዚህ ዓመት አለማረሳቸውን ተናግረዋል። ቀደም ሲል ተፈጥሮ በነበረ ሁከት የወደመ ሰብልና ንብረት ካሣም እንዳልተከፈላቸውና ይህም ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ዶክተር ሲሳይ ምህረቱ የአምቦ ከተማ ነዋሪ ነው። የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያና መሸጫ ድርጅት ባለቤትም ነው።
በሰንቀሌ ፖሊስ ማሰልጠኛ የሚገኙ አንዳንድ የታሰሩ ግለሰቦች በምግብ እጥረትና አያያዝ ጉድለት እየታመሙ መሆናቸውን ገልፁ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ