በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤኒሻንጉል ጉምዝ የሚገኙ ባለሃብቶች ሁኔታ


በቤኒሻንጉል ጉምዝ በሎ ጀጋንፎይ ወረዳ ውስጥ በግብርና ሥራ ላይ ነዋይ አፍሳሽ የሆኑ አንዳንድ ባለሃብቶች በፀጥታ ስጋት ምክንያት በዚህ ዓመት አለማረሳቸውን ተናግረዋል። ቀደም ሲል ተፈጥሮ በነበረ ሁከት የወደመ ሰብልና ንብረት ካሣም እንዳልተከፈላቸውና ይህም ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በሎ ጀጋንፎይ ወረዳ የሚገኝበት የካማሺ ዞን አስተዳዳሪ በበኩላቸው ባለፈው መስከረም የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ጥቂት ባለሃብቶች ንብረታቸው በመውደሙ በአሁኑ የመኸር ወቅት ሥራ ላይ መሠማራታቸውን ጠቅሰው፣ ሁኔታው በዞኑ ምርትና አቅርቦት ላይ ጎጂ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ለችግሩ መፍትኄ ለማበጀት ከክልልና ግጭቱ ከተፈጠረባቸው አዋሳኝ ዞኖች ጋር እየሠሩ መሆናቸውንም ለቪኦኤ አስታውቀዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በቤኒሻንጉል ጉምዝ የሚገኙ ባለሃብቶች ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:06 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG